Sunday, January 17, 2021
Home Blog

የአስቆርቱ ይሁዳ

2

የአስቆሮቱ ይሁዳ፥ አጥቅሶ አብሮ እየበላ የሚያዋውል፥ስሞ የሚጠቁም፥ ኮሮጆ ይዞ የሚሰርቅ፥ እየተከተለ የሚከዳ፥ ደቀመዝሙር ተብሎ ከፈሪሳዊ የሚውል ዳተኛ! ያጎረሰውን እጅ የሚነክስ፥ እየተማረ ወደ እውነት የማይደርስ፥ በንፋስ የሚወሰድ ውሀ የሌለው ዳመና፥ ፍሬ የማያፈራ ሁለት ግዜ የሞተ፥

ከስሩ የተነቀለ የበጋ የደረቀ ዛፍ፥ የገዛ ነውሩን አረፋ እየሚደፈቅ፥ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀለት የሚንከራተት ኮከብ- አስቆሮቱ ይሁዳ!

የሀያው አመት ቆሞ ቀሩ የራሻ ኢኮኖሚና ሚካኤል ጎርቫቼቭ

——————————————-

ለሀያ መት በኢኮኖሚ ቆሞ ቀርነት የተቸገረችው ራሺያ ተስፋ እንደ ሰማይ በራቃት ግዜና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ በምትርመሰመስበት ግዜ ላይ በድንገት ልጅ እግር የሆኑት እንደኛው እንደዛሬው አብይ አህመድ፥ ብዙ ተስፋ ተጥሎባቸው በድንገተኛ በሚመስል ሁኔታ በዋና ፀሀፊነት በኮሚኒስት ፓርቲ ላይ ተሹመው ወደ ስልጣን በመንደርደር መጡ- ሚካኤል ጎርቫቼቭ! 

ጎርቫቼቭ ምንም እንኳ ኮሚኒስት ቢሆኑም ቅሉ የራሳቸውን ሀሳብ በግል የሚያጠናጥኑ እንደሆኑ ይነገርላቸው ነበር:: ልክ እንደ አብይ ኦህዴድ ቢሆንም፥ ከኦዴድነት በፊት የህውሀት ግርፍ ቢሆኑም ግን የለውጥ ሀዋሪያ ናቸው እንደምንለው ሁሉ……..

ጭቃ ነው አፈር ነው ምን ብታላውሰው

ብረት አይላበስ አይዝግም ፈራሽ ነው

ከስሪቱ ውጭ እንዴት ይሆናል ሰው 

ጎርቫቼቭ የራሺያን የሀያ አመት የኢኮኖሚውን ስንቃር የምጣኔ ሀብት መፍትሄዎችን ሊፈቱ ሁለት መላ ባይ መፍትሄ ይዘው ብቅ አሉ:: ይኸውም Perestroika እና Glasnost በመባል የሚታወቅ ሲሆን ትርጓሜውም የተሀድሶ (reform/restructuring) እና ግልፅነት (transparency/political openness) የሚል ሲሆን ለዚህም ተሀድሶና ግልፅነት መላ ምት አጋና ተመታ:: ራሺያውኑ ማጨብጨብ ጀመሩ! ከሀያው አመት የኢኮኖሚ ወጠምሻ ድንቃር የሚያወጣቸውን መሲህ እንዳገኙ አሰቡ:: በተሀድሶ ፈረስ የበሰበሰ ስርአታቸውን ሊያድሱ፥ በዛው በድሮው በሬ ሊያርሱ የብሬዥኔቭ መወገድ ብቻውን የችግሩን ስር ቀራፊ አድርገው በምናባዊ ጎርቫቼቭ አፈ ጮሌነት የቃላት ጋጋታ ተታለሉ ልክ እደዛሬው እንደኛው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አይነት ተስፋ ቢስ ባዶ ቃላት ተሸነገሉ:: የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ነውና ነገሩ……ጎርቫቼቭም አንዳንድ ነገሮችን ዞር ዞር አድርገው ማስቀማመጥ ጀመሩ:: የዛሬይቱ የኛው አገር የወያኔን መዋቅር ይዘን አንድ ሰው “ጌታቸው አሰፋ ይያዝልን” እንደምንለው ያለ ውጥንቅጥ በራሺያም ነበሩ ኮምኒስት በተባለ የሰው ልጅ እኩልነት አንጋች ውስጥ የበሰበሱ ቱጃሮች በሙስናው ጭምልቅልቅ ያሉ ነበሩና:: ጌታቸውና ግብረ አበሩ እኮ የሰሩትን ሁሉ የሰሩት አሁን ኦህዴድ፥ ብአዴን፥ኦህዴን ወዘተ የተባለን ድርጅት መስርተው በዚያውም ውስጥ ከአብይ ጀምሮ ሰዎችን አሳድገው፥ ሆድ አደረሮችን በገዛ ወንድሞቻቸው ላይ አስነስተው ነው እኩይ ተግባራቸውን የፈፀሙት:: በተለይ በተለይ ደግሞ ብአዴን የሚሉት የቤት ባሪያው የብዙ አማራ የስቃይ ሰለባ መሆን ዋናውን ሚና የተጫወተ እየተጫወተም ያለ፥ ትናንት ለህውሀት ዛሬ ለኦነግ ግልገልነት ገብቶ የአማራን እንቅስቃሴ እየመዘመዘ እንደ ምስጥ ከውስጥ በልቶ ሊጥል ሽፋን (front) እያበጀ አማራዊውን ማእበል ለማዳከም ሌት ደቀን ሽር ጉድ እያለ የማይቀዝፍበት መቅዘፊያ የለም!በዚህ ጉዳይ ስናንነፃፅረው ኦህዴድ ምንም ግርድና ውስጥ ቢሆን ኦሮሞአዊ ገረድ ነበር! እዚህ ላይ ይሰመር! በኦህዴድና ኦነግ መሀል ያለው ልዩነትም የዛው የአንዱ ሳንቲም ሌላ ገፅታ መሆን ላይ ብቻ ነው! ኦህዴድ በ”ኦሮሚያ” ላይ በራሱ ጤና ጣቢያዎች ሴቶች ልጆች አምካኝ መርፌ አላስወጋም! ብአዴን ግን አማራ ስላልሆነ በሆድ አደር የቤት ባሮች እጅ ያለ ድርጅት ስለሆነ ልጃገረዶችን በመርፌ ያስመከነ እኩይ ነው! የአስራ ሁለት አመት ልጃገረዶችን ያመከነ ድርጅት ነው! የትናንቱን በጎጃም የተደረገውን ብቻ እንዳታስቡ ዛሬ በሸዋ አማራ ልጃገረዶች ላይ የማህፀን ካንሰር መከላከያ ክትባት በሚል አሁን ይህንን እያነበባችሁ ልጆቻችንን በዚህ ዘር ፅዳት እያስቀጠፈ የሚገኘው ይሄው የቤት ውልድ የቤት ባሪያ ብአዴን ነው:: ብአዴን በስናይፐር ባህር ዳር ላይ ከመቶ በላይ እምቦቀቅላ ልጆቻችን በአንድ ጀንበር ጭጭ አድርጎ የጨረሰ ድርጅት ነው:: ከራሱ ፅህፈት ቤት ጣሪያ ላይ መሽቆ እንደቆሎ የሰው ክቡር ህይወት ሊያውም ያማራውን ደም እንደጎርፍ ያፈሰሰ የቃየልን መንገድ የሄደ የአማራዊያን ደምም ዛሬም ወደ ሰማይ እየጮኸ ይገኛል! በአንድ ጉድጓድ ከሰማኒያ በላይ ልጆችን እየገደሉ ቀብረዋል:: ዛሬም እንደትናንቱ የባርነት ግዳጁን ሲወጣ የአማራን ብሄርተኝነት ሊያዳፍን “አማራ ዘር አይቆጥርም” ይለናል የተሰጠውን ክልል በቅጥ ሳይመራ ዳያስፕራ ሊደሳኮር በየአሜሪካኑ እየዞረ በጀት እውጥቶ ቬኬሽን ሽርሽር ላይቭ ከፍቶ ይወስዳል፥ በተራበ በታረዘ ወገናችን ሂሳብ:: እዚህ ያለንበት ድረስ መጥቶ ደግሞ ያፍ ለከት ባጣ ለበጣ “ችግር አለብን” “መሻሻል አለብን” እያሉ አፌዙብን:: አማራ ተብየውም ቁጭ ብሎ ይህንን ብልግና ይሰማል፥ ይሰደብበታል! አማራ ዘር ካልቆረ ታዲያ አንተ አማራ በሚል አገርና ህዝብ ተሹመህ ስለምን ትሰራለህ? በአማራ ምድር አማራ ርእሰ መስተዳደር በሚል ደሞዙን እየበላ፥ ሰው እንደቅጠል ሲረግፍ ቃታውን የሳበ የቤት ባሪያ “ዘር አንቆጥርም” ሲል ተሰምሯል ባይሆን ትንሽ የውጭውንም አለም exposure አለው የተባለው የማህበረሰቡ ክፍል ዝም ብሎ ይህንን ስድ ቡድን ይሰማዋል:: በጩኸት እንኳን ለአፍ ገደብ ማሰጠት ያቃተው ዳያስፕራ:: “አማራ ዘር አይቆጥርም” ማለት “አማራ የለም” ከሚለው ምፀት የሚለየው ምንም ነገር የለም! እንዴት ይህንን ህዝባችን እየሰማ ቁጭ ብሎ ይሰደባል ብለን ስንጠይቅ መልሱ ፖለቲካችን ሳይንስ ስላልተላበሰ ነው:: አዎን የአማራ ፖለቲካ ሳይንሳዊ አይደለም:: የአማራ ፖለቲካ እድር ቤታዊና እቁብ ቤታዊ ነው:: ሲለውም ፀበል ፀዲቅም ይሆናል:: ልጆቹ እየተቀጠፉበትና ጠላት በምድሩ ተደራጅቶ 70 ቀበሌ አምጣ ሲለው በታቦት ይዳኛል! ወይንም ገንዘብ ይሰበሰብበታል አሊያም አዳራሽ ሞልቶ ድንኳን መስፊያ ዘዬ ይቀየስበታል:: ሰው ሲሞት ማን ጡሩንባ ይንፋ አይነት ጉዳይ ይባባልበታል:: የኢ-ሳይሳዊነታችን ማሳያውም በአዳራሽ እየሞሉና እየተሰበሰቡ ጥያቄና መልስ ከአሳሪዎቻቸውና ከአሳሳሪዎቻቸው ምላሽና መላን መጠበቁ ላይ ነው:: አማራ ሆይ ትግሬው ወያኔ የሾመላችሁን ሰዎች እናንተ ከእራሳችሁ ለማውረድ እስካልቆረጣችሁ ችግራችን መልኩን ይቀይራል እንጂ ችግሩ አይቀረፍም! አንድ ግዜ ነው አሉ ሁለት ጓደኛሞች ጠንቋይ ጋር ይሄዱና የሚሆነውን ነገር ለአንዷ ጥሩ ጥሩ ነገር ነገራት በተራ ቁጥር:: መጀመሪያ ታገቢያለሽ፥ ንግድ ትከፍቻለሽ፥ ከዛ ትወልጃለሽ ቀጣጠለላት:: ለሁለተኛዋ ደግሞ አንድ ነገር ብቻ አሁን ያሰበችው ነገር እንደማይሳካ ነገራት:: ግራ ቢገባት ለኔም ዘርዘር አድርገህ ንገረኝ እሺ ይሄኛው ጉዳይ አይሳካም ሌላው ቀጣይን ስትለው….. እ እ ለዛኛውም ጉዳይ ስኬት አላይም አላት:: እሺ ከዛስ ስትለው ከዛማ ችግሩን ትለምጂዋለሽ አላት አሉ:: አማራም ይህንን ብአዴን ችግሩን ከራሱ ላይ ካልጣለ ችግር በያይነቱ ይሆናል ምግቡ:: እግዚያብሄር ይጠብቀን ከዚህ!

መለስ ዜናዊ እነ ገዱንና ግብረ አበሩን በበረከት ሲሞን አማካኝነት ሲመለምል አጢኖ ነው:: በራሱ መቆም የማይችል ወኔ ቢስ ሆድ አደሩን መርጦ መርጦ ነው:: እንዴት እንደሚመለምሏቸው ባውቅ ደስ ባለኝ ለእኛም ለይተን ከመሀላችን ለማውጣት በረዳን ነበር:: 

The Gorbachev factor

———-///————

 ትናንት እንደተናገርኩት ዛሬም የምደግምላችሁ ተሀድሶ ሲባል ለውጥ አይጠበቅም! ተሀድሶ ሲሉህ የነበረው የገማው ያንኑ ስርአት ሽታው ከዚህ በላይ እንዳይቀረናህ ዲዮድራንት ይቀባል ማለት ነው:: ባልታጠበ ብብት ዴዮድራንት ሲጨመር ደግሞ ቅርናት አይነቱን ይለውጣል እንጂ ንፁህ ንፁህ አይሸትህም:: ያልታጠበውና ዲዮድራት የተቀባው ብብት ቅርናቱ ይበልጥ ይበልጥ ነው፥ ያጥወለውላል:: ለውጥ ይመጣል ብሎ ማንም ተስፋ አልገባልህም አንተ ግን ያው ስለጨነቀህ ልጁ የኔ ነው ብለህ ልታሳድግ እርጉዝ ማግባቱን መርጠሀል እናም አብይ የኦህዴዱ አንበል የወያኔ ጡት ልጅ በራስህ ዘይቤ “ኢትዮጵያ ፌንት አድርጋ ነው እንጂ፥ ኮማ ውስጥ ናት እንጂ እንጂ እንጂ አልሞተችም” የሚል ስላቅን ቀዝቃዛው በድኗን ተሸክመህ እያራደህ በውሸት ተስፋ በዝላይ ትሟሟቃለህ:: ግን በድኑን እስካላወረድክ ድረስ በዝላይ እየተሟሟቅህ በበድኑ ቅዝቃዜ መንዘፍዘፍህ አይቀሬ ነው:: ተሀድሶ ስትባል የነበረውን ያው በጌታቸው፥ በስብሀት ወዘተ ያንገሸገሸህን ስርአትን ማደስ ወይንም በፈረንጄው አፍ facelift መስጠት ማለት ነው::  ጠበቅ ማድረግ!  ትግሬ ፀረ-አማርነትን ወደ ኦሮሞ ፀረ- አማራነት ይቀየራል ማለት ነው ባጭር ቋንቋ! 

እናም የራሺያ ትንንሽ የንግድ ተቋማት ሬስቶራንቶች፥ እህል ገበያው ወዘተ ትንሽ ሞቅ ሞቅ አለላት:: ንግድ አውታሮች የራሳቸውንም ዋጋ ተመን መስጠትና ትርፍን ገደብ ማግኘት እንዲችሉ ንግድ አውታሮች ለጥቂት ተበረታቱ እናም ቀና ቀና ቀና ማለት የሚጀምሩ መሰሉ:: እኛ አገር ፒዛ ሀት እንደከፈቱልን በአብይ መምጣት ማግስት ለራሾቹም ሜክ ዶናልድስ ተከፈተላቸው:: ያይጥ ይሁን የድመት ስጋ የሚሸጠው የማይታወቀው ማክዶናልድስ መከፈት ከለውጥ የቆጠረ አይጠፋል ልክ እደኛ 800 ብር ፒዛ በአገሩ ላይ መሸጥ እንድገት የሚመስለው እንዳለው ሁሉ:: ያው የራበው ህዝብ መሪውን ሊያኝክ ስለሚችል ለጠኔ ማስታገሻ ትንሽ ለቀቅ ለቀቅ አለ:: ሆኖም ግን በብዙ ዋና ዋና በሚባሉ ንግድ አውታሮች ላይ የነበረው የዋጋ ቁጥጥር አለመነሳትና የትርፍ ገደብ አድማስ መከለል ተስፋ የተጣለበትን ኢኮኖሚ በጨቅላነቱ ቀጨው:: የታሰበው ለውጥ አልመጣም:: እንግዲህ ይህ ሲሆን ልብ ልንለው የሚገባ Perestroika ወይንም Restructuring በሚለው ሽፋን አንዳንድ ነገሮች መቀየራቸውን ነው:: እነዚያው ጉበኞች፥ ለራሳቸው ጥቅም የሚቆሙ ፖለቲከኛች መሀል መዟዟር ተደረገ:: እንደኛው የዛሬይቱ ኢትዮጱያ! ለውጡም አልመጣ ግልፅነትና ተሀድሶውም ሳይመጣ ልትወጣ የመሰለችው ፀሀይ ተመልሳ ጥልቅ አለች::  ወደ ለመደው ድድቅ ጨለማ ኩራዙን አብርቶ ሊቀመጥ ህዝበ ራሺያ አዘገመ:: ከፊተኛው ይልቅ ያሁኑ ስብራት ብሷልና አንገት መሬት ነካች:: እነዚህ self-serving ኮሚኒስት ፓርቲ አባላት ሌላ ተስፋ ወረወሩ ዲሞክራታይዜሽን የሚል:: ሌላ ስላቅ! የራበው ምግብ እንጂ በባዶ ሆድ አውራ ብትለው አቅሙስ ከየት ይገኛል?! 

እንዲህ ስፍገመገሙ የነበሩት ጎርቫቼቭ የማሉበትን ለውጥ ማምጣት ቢሳናቸው በዲሞክራታይዜሽንና Glasnost ወይንም openness በሚል ግልፅ ውይይቶችን በማበረታታት እንደዛሬው እንደኛው አገር ያለ ክርክሮችን በምሁራን መሀል እንዲደረጉ ያበራታቱ ገቡ:: ህዝብ በወሬ፥ በሀሳብና በቲዎሪ ተጠፈረ! ተንፍሶ የማያውቅ ህዝብ ደግሞ እድሉን ሲያገኝ አውርቶ አይጠግብም! እኛም ዛሬ የወደፊቱን እንዳናስብ፥ አገር ወዴት እየሄደች ነው እንዳንል ይህ የምናየው ለውጥ ወይስ ነውጥ ብለን እንዳንጠይቅ ብዙ የቲቪ መስኮቶ ተዘጋጅተው በዶክመንተሪና የመሳሰሉት እንደ “አዲሳባ የማናት” የሚሉ የጅሎችና ታሪክና አገር የማያውቁ የአጉራዘለል መድረኮች እየተበራከቱ እያየን ነው ያለነው!አዋቂዎች ሳይሆኑ ተምረው ያልተማሩ ወደ እውነት የማይደርሱ ሰዎች መደረክ ተከፋፍቶላቸው የህዝብ ንቃት ህሊናን እያጋሸቡ ይገኛሉ:: 

እናም ጎርቫቼቭ ያሉትን የምጣኔ ሀብት ለውጥ ማምጣት ሲሳናቸው “radical reform” ብለው ደግሞ ተሀድሶውን አክራሪ አድርገው አመጡት:: ዛሬ ዛሬ እኮ የፖለቲካችሁ አባባ ተስፋዬ ጠ/ሚ አብይ “ዋ ዲክቴር ልታደርጉኝ ነው” የሚል ለሁለተኛ ክፍል ተማሪ የማይመጥን ስላቅ ፖለቲከኞች ነን ባዮችን ሰብስቦ ነው የሚሰለቀው:: ይሄ እኮ አገራችንና ህዝቧ የደረሰበትን የንቃተ ህሊና ዝቅጠት የሚያሳየው እንጂ ሌላ አይደለም! የአምባገነን ሬሲፔ አለኝ እያለህ ነው! አንተ ታጨበጭባለህ! ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እውነት አለው ጭብጨባ ያስብዳል ይላል:: አብይንም በጭብጨባ አሳብዳችሁት አገር ላገር ጭብጨባ ኪኒኑን ፍለጋ ህፃናትን ሳይቀር መጠቀሚያ አድርጎ የፎቶ ሚኒስትርነቱን ተያይዞታል እድሜ ላሳባጁ አጨብጫቢው ህዝባችን! እሱ እንደው ለግለ ስብእና ግንባታ እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ ነው:: ለሶስት አስርታት ግን ፈርሳና አገርነቷ ቀርቶ ብዙ የምእራባዊያን የፖለቲካ ቁማር ያስተናገደች ሶማሊያ እንደገና ተሰርታ ተውተርትራ ቆማ በፖርላማዋ ጠቅላይ ሚንስትሯን መሀመድ ሙርሴልን impeach ልታደረገው እንደምትችል እያርበደበደች ከኢትዮጵያውና ኤርትራው መሪ ጋር የተዋዋለውንም ያደረገውንም ስምምነት ሚስጥራዊነት ባስቸኳይ እንዲገለጥ ብላ ሽንጧን ስትገትር ሳይ ወይ አገሬ አሰኘኝ:: ሶማሊያዊያኑ ማሰብ አላቆሙም፥ ለሰው አይስግዱም ግን በአመክንዮ ይሞግታሉ:: ታዲያ ፈርሳ ለዚህ መጠገን ሶማሌ ስትበቃ አለች የተባለች ኢትዮጱያ ሞታ ከደነዘዘች ምንድነው መኖር አያሰኝምን?! 

ጎርቫቼቭ ብዙ ጠመዝማዛ መንገድን ሲቀይሱና ሲያወናብዱ ከምእራባዊያኖች በራሺያ ላይ ሲዋዋሉ እራሺያ ልትፈርስ ጀመረች! እንደኛው እንደዛሬው ሊብራል ኢኮኖሚ እሳቸውም ይህንን መሰል ቁማር ጀመሩ! ሀብታም እያካበተ ደሀም እየደከረተ ሄደ::  ራሺያ ተስፋ ወደሰማይ አምጥቃ እንደርችት ልትለኩሰው ብልጭታ ስትጠብቅ እንደኔዋ እንደዛሬዋ ኢትዮጱያ ርችቱ ሳይበራ ጨለማን መሰወሪያው አድርጎ ተውጦ ቀረ!  ጎርቫቼቭ ስልጣን ገደብንና ቅነሳን  በባለስልጣን አመራሮች ላይ አደረጉ:: ይህ ሚሊተሪውንና አዛዦችን ከአገራዊ ህላፊነት ገለል የማድረግ ስራዬ ይመስላል:: ወደፊትም ምርጫ  ብዙ ተወዳዳሪዎችን ያማከለ በሚስጥር (secretive ballot) እንዲሆን አበረታቱ:: እነዳዛሬዋ የአብይ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚውን ለማንሳት ጎርቫቼቭ ነፃ ኢኮኖሚንና በትልልቅ የንግድ አውታሮችን ወደ ግለሰብ ይዞታ ለመለወጥ እቅድ ነደፉ ይኸው እቅድ ግን ራሺያን ኢኮኖሚ ላንዴም ለመጨረሻ መቀመቅ የከተተ ነበር:: ከብሬዥኔቭ ከነበረው ምግብ እና ቁስ እቃ አቅርቦት እጦት በጎርቫቼቭ ባሰ! በነገራችን ላይ አብይ ከመጣ “ዝርፊያ ከቆመ” ኃላ የአንድ ነገር ዋጋ የቀነሰ አለን?!  የደከረተ ስራ ሲፈታ ፖለቲካ ውስጥ የገባ የዲጄዎች ፖለቲከኞችን ወደ አገር በመንግስት አበል እንደተወሰዱና ሆቴሎቻቸውና ምግባቸውን ሁሉ እንደተቀለቡ ግን ሰምተናል:: ለአብይ መንግስት ለራሱ ገፅታ ግንባታ ይህ ሁሉ የአገር ገንዘብ ሲባክን ጉዳዮን ያጤነ የለም:: ጎርቫቼቭ በዚህ በርሊን ግንብ ያፈርሳሉ ያስፈራርሳሉ እዚያ አገራቸው ግን አገር መፈራረስ ጀምራለች:: ልክ እንደኛዋ እንደዛሬው ከኤርትራ ጅቡቲ፥ ሶማሊ ታንዜኒያ እንደሚዞረውና አገርን ድንበር የለሽ ለማድረግ አገራትን እናተልቃለን ዳር ድንበርን በመሸርሸር ተብሎ እንደምንጋተው ጠቅላዪ እየዞሩ የሚፈርሙበትን ሰነድና ውል ባናቅም ቅሉ አገራችን ግን ከትናንቱ ዛሬ በባሰ ሁኔታ አገራችን ውስጥ የዘር ፍጅት፥ በየአካባቢው ግጭት እንደምናይ ሁሉ ራሺያም ሚሊተሪ ስር አትመጣስና አቅሟን የፈተነ ችግርና  ግጭቶች መበራከት ጀማመሩ:: የታሪኩን ሂደት እዚህ በዝርዝር ማስቀመጥ ግዜ ስለማይፈቅድ በግርድፍ ይህንን መሳይ ሂደት “አንድ አገር” በሚል ትርክት ሚካኤል ጎርቫቼቭ አገር እያታለሉ በዚያ በርሊን ግንብን ሲያፈርሱ በዚህ አገራቸውን የምትፈርስበት ገደል ጋር ጥደው ነበር:: ዛሬ ከኬንያ፥ ኤርትራ፥ ሶማሌ፥ ጂቡቲ ጋር ሆነን ወደቡ ግመል ማሰሪያ ከሚሆን አንድ መርከብ ከሚያስተናግድ ይልቅ አንድ ሆነን ብንጠቀምበት” እያለ አብይ እቃ እቃ ይጫወታል በአገርና በህዝብ ላይ በዚያ ግን አዋሳ ላይ ሰው ይታረድል: እዚህ ቤኒሻንጉል ላይ ሰባ ሺህ ሰው ተፈናቀለ እንባላለን:: ሰባ ሺህ ሰው እንዴት ይፈናቀላል ጃል? ሰባ ሺህ ሰው እኮ አንድ ከተማ (town) ነው:: ይህንን ያህል ቁጥር ያለው ሰው ተነስ ብለህ ሞብላይዝ ለማድረግ በክክል ደረጃ ሳይሆን በፌደራል ደረጃ ያለ ሀይል ተጠቅመሀል ማለት ነው:: ለምን አስፈለገ ከገዛ መተከል ምድሩ አማራውን ማፈናቀል? ሌላው ሸፍጥ! ሚዲያን ተገን ያደረገ በcontroled oppositions መገናኛ ብዙኃን አስተባባሪነት ሲያስለምዱት የነበረ የተሰራም ያለ ሸፍጥ::

ሚዲያ ሸፍጥ (ኢስትና ኦነጋዊ ህውሀታዊ ፀረ-አማራዊ ሸፍጥ)

——————————————

ኤርሚያስ ለገሰ ዋቃጂራና እነሀብታሙ በትግሬው መንግስት ስር ብዙ ያገለገሉ ናቸው ወደ ዳያስፕራ ከመላካቸው በፊት! ዋና የሀብታሙ ታርጌት አማራ ትግል ነበር ለሚያስታውስ:: የበረከት ሲሞን ቅጥረኞች ሲል አማራዊ ሰደድ እሳት በጆግ ውሀ ሊያጠፋ ሲዳዳው ተላልጦ ጥጉን ያዘ:: በዚያ ግን አላቆሙም ህዝብ ወደ ማደናገር ስራቸው ገቡ የኛን ሰደድ ወላፈን ቢያቅታቸው:: ኤርሚያስ በትግሬው ደብል ኤጀንትነት እንዲኮበልል በተደረገ ማግስት ሰተት ብሎ ኢሳት ነው የገባው:: ምን ኢሳት ያልገባ ማን አለ ዳዊት ከበደም ኢሳቴ ነበር ባንድ ወቅት! ወያኔ ጢባጢቢ የተጫወተችበት ትልቁ ልጅነቷ ወራትን ማን ይዘነጋል:: በደብል ኤጀንቱ ኤርሚያስ መጀምሪያ ያደረገው “የመለስ ልቃቂት” በሚል ያሳተመው መፅሀፍ በስስ በስሱ የኢትዮጵያ ነገር ያለቀለት ነገር ነው የሚል እድምታ ያለው ሲሆን የራሱንም የወንጀል ተባባሪነት ሳያውቅም ይሁን አውቆ ከማሳየት በላይ ፖለቲካውን በሳይንስ ለሚቃኝ ያደረገው ነገር የወያኔን አሰቃቂ ድርጊቶችን normalize በማድረግ ስነልቦናዊ ጦርነትን ነው ያካሄደው:: ኤርሚያስ ዋቃጂራ በዋናነት አዲስባን ከወያኔ ጋር ሆኖ social engineering እንደተካሄደ ሲገልፅልን አልቆላችኃል ሲለን ሲሆን እኛ ደግሞ አልቆልናል በሚል ቁጭ ብሎ የሱን ትረካ ሰሚ የማድረግ ስነልቦናን የማኮላሸት ስራን በስነልቦንችን ላይ ሲሰራ ተስተውሏል:: በመቀጠል አበክሮ የሰራበትና brainwashing ታክቲክ በመጠቀም ኢሳት ሚዲያውን በመደገፍ የሰሩት የ”ታላቋ” ትግሬን እቅድና ካርታ በስልታዊ መንገድ ማስተዋወቅ ነበር::  ልክ ግን ወያኔ ዛሬ በማሊያ ጭልጋ ላይ ጭፍጨፋዋን ስትጀምር ይህንኑ ያስተዋወቁላትን እቅድ ልተገብር ስትነሳ ኢሳት ካሜራዎቿን አጠፋፍታ media blackout treatment ለነገሩ ለግሶን ዝምታ ነው መልሴ ብሏል:: ከዚህም ቀደም በመሰል ጉዳዮች ላይ selectively ለነሱ በሚመቻቸው መንገድ ለግምቦት ዜሮ ፖርቲያቸው ትግል አየር በአየር ሲነግዱ “ዲሽቃና ዳባት” ላይ ነን የሚል በሬ ወለደ ውሸት አይናቸውን በጨው ታጥበው ሲዋሹ ሀፍረት ሳይዛቸው ነው:: ዛሬ ካርታ እያሳየ እስከ ጋምቤላ መውጫ እንዳበጁ የተረከው ይኸው የወሬ ጣቢያ ጭፍጨፋውን ህውሀት በአብይ አፍዝ አደንግዝ ሸፋኝነት ስራውን ስትጀምር አዲስ ቤተ ሰሪነቷን የወሬው ጣቢያ ካሜራውን ሌላ ማጉሊያ አስገብቶ አጥብቦ አጀንዳ የማስቀየስና የማራገብ ስራ ውስጥ ተጠምዷል:: የቤኒሻንጉል ከመቶ ሀምሳ ሺህ በላይ ሰው ባለፉት ስድስት ወራት መባረርና በጎንደር ጭልጋ ድረስ ገብቶ የማፈናቀል ስራ ብሎም በራያ የሚያሳየን ቤተ ሰሪዋ ህውሀት አገር ቆርሳ ልትሄድ ደፋ ቀና ላይ መሆኗን ነው:: አገር የፈረሰች የጆትጅ ሶሮስ ስሪቶች ደግሞ ስለአብይ ሸሚዝና ስለበረከት ሲሞን ፀጉር አቆራረጥ አይነት ወሬ ይሰልቃሉ እሹሩሩ ይሉሀል እንዳትነቃ ከእንቅልፍህ! 

ትግራይ በአሁኑ ሰአት ተገንጥላለች:: ይህንን በጡሩንባ እስኪነገርህ የምትጠብቅ ፖለቲካን በእድር ቤት ትርክት ኢሳት አይምሮህን ያበላሸ ስትሆንና “ኢትዮጵያ ፌንስት ሰርታ ነው እንጂ” የሚል የአብይን ተረት እያነበብክ የምታንኮራፋ ስትሆን ብቻ ነው:: ካልሆነማ እስኪ ወንድ ነኝ ያለ ትግራይ ይሂድና ጌታቸው አሰፋን ያውጣ? ልዐላዊት ትግራይን መድፈር ያቃተው ማእከላዊ መንግስት ማእከላዊ መንግስት ሳይሆን ጥጋዊ መንግስት አድርጋዋለች ህውሀት! 

እናም ልክ እንደዛሬዋ ትግራይ በድብቅ ባይሆንም ሉቴኒያ በግላጭ የመጀመሪያዋ ጎጆ ወጪ ጫጉላ ቤቷን ሰራች! ባይ ባይ ራሺያ ብላ ሄደች! ከተፈራረሙብትን Warsaw pact ጥላ NATOን ተቀላቀለች:: ራሺያ ፈረስ ፈረስ ማለት ጀመረች:: ራሺያ በ1955 በስምምነት በተፈረመው Warsaw Pact የራሺያን የሚሊተሪ መስፋፋትን ገደብ ያደረገ ቀድሞ የተደረገ ስምምነትን እየጣለ ሁሉም በያቅጣጫው ቤቱን እየሰራ መቆረስ ጀመረ:: 

ይህ ሁሉ ሲሆኑ ወደ አምስት አገራት የሚሆኑ እንደ ካዛኪስታን ያሉቱ አገር መፍረሷን የሰሙት ወይንም የታያቸውና የታወቃቸው ሁሉም ተገንጥሎ ሲያበቃ ነው:: አንድነት በሚል ትርክት ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበሩና እነ አዘርባጃን ካዛኪስታን ታዥኪስታን ኡዝበርኪስታን መጨረሻ ሁሉም ሄዶ የቀሩት የበሩ ናቸው:: ዛሬም አማራው የዚህ አይነት ጉዳይ ውስጥ ያለ ይመስላል:: ትግሬ ከአማራ በወሰደው መሬት ላይ አምቧጓሮ አንስቶ በማናለብኝነት ሲፋንን መሄጃው ስለደረሰ ነበር:: ኦሮሞው ፊንፊኔ እያለ አዲሳባን በአንድ መንደር ስሟ የራሴ ነው ብሎ አገር ይያዝልኝ ሲል ምክኒያቱ ግልፅ ነው:: መቼማንድ ሆኖ አገር ለመቀጠል ቢሆን ኖሮ ጉዳዩ በአዲሳ የማናት በሚል ጉንጭ ባለፋ ነበር ግን እነሱም እንደትግሬው ይዘው ሊሄዱ ጥሎሽ ስጡን ነው ጉዳዩ! ሶማሌና ኦሮሞ አገር አንድ ብትሆን law of order በቦታው ቢሆን ሞያሌ ላይ ምን ያስጨራርሳል?! የኔ ነው የኔ ነው ድንበር ሲሰመር ነው:: 

ጎርቫቼቭ ባለብዙ ተስፋ ሰጪው የጠነከረ የህዝብ ጉምጉምታን አስመልክተው አገሪቱ ወደ ማትወጣበት ውጥንቅጣ ሳትገባ በፊት ብለው ስልጣናቸውን በውዴታ ለቀቁ:: እውነታው ግን ጎርቫቼቭና የልሲን ህዝቡን አሳውረው የራሺያን መበተን ጨርሰዋል በውስጥና ነው:: አብይም ትንሽ ቆይቶ አገር መረጋጋት አልቻለም እኔም አቃተኝ ይላል ወይን በሌላ ጉዳይ ከስልጣን ዞር ማለቱ አይቀሬ ነው :: ምክኒያቱም በአሁኑ ሰአት እንኳን ዜጎች እርሱ እራሱ እንኳ ወለጋ መሄድ ሞት ሊያመጣበት እንደሚችል ተናግሯል:: ይህ ምንን ያመላክታል? ወለጋ ውስጥ ታጣቂውና ሰውን ቁጭ ብድግ የሚያደርገው ኦነግ መሆኑ ይሰመርበትን ትግራይ ያው ግልፅ ነው ብዬ ነው! ትግራይ ላግዠሪ ላይ ትመስላለች:: ዲሞክራሲ ውገቧን እየፈታተሸችባት ይመስላል: ለኛ ተሰብስበው በአማርኛ ይደሳኮራሉ:: ለወትሮው እኛ ስናቅ ስብሰባ ሁሉ በትግርኛ ነው:: በአማርኛ የሆነ ስብሰባ ይህ ነገር ለኛ ነው ብለን እንሰማ ዘንድ ነው:: ሶማሌም ዛሬ በነበረ በተባባሰ የፀጥታ ችግር ምክኒያት ወጣቶቿን እንዲደራጁ አዝዛለች! የተሾመባቸውንም ሰው ጥበቃ አላደረግህልንምና ከዚህ ኃላ አንተን አንፈግም ብለዋል:: አብዲ ኢሌ በዚህ ጨዋታ የተበላ ይመስላል! ኦሮሞዎቹ በስልት እጃቸው አስገቡት:: የራሳቸውንም ሰው ሶማሌው ላይ ሾሙ ጎጆ ውጪ ላይ ችግር እንዳይገጥማቸው!  ኦጋዴንን ያለ መሪ ያስቀሩት ይመስላል:  

አማራ ሆይ ኢትዮጱያ በመስጠም ላይ ያለች መርከብን ትመስላለች! አሁን አብይ፥ አንድነት፥ ገለመሌ እያልክ አገር አልባ ሆነህ እንዳትቀር በቶሎ እራስህን ከምናባዊ አለም አውጣና ዝዙሪያ ገባውን ቃኘት ቃኘት አድርገው:: ይታያል ብዙ ሳታተኩር! 

አገራችን በመፍረስ ላይ ያለች አገር ነች! ልትፈርስ ነው አላልኩም! በመፍረስ ላይ ነች! 

የጂፕሲነትን እጣ እንዳይደርስብህ መሳሪያህን ቶሎ ወልውል:: በመገናኛ ብዙኃን አፍዝ አደንግዝ ዜና አትጠመድ:: እራስህ ቃኘው አገሩን ነገሩ ግልጥ ነው! 

አብይ የኛ ጎርቫቼቭ መሆኑ ነው! ምእራባዊያኑ ጎርቫቼቭን ብዙ ውዳሴ ቸረዋቸው ነበር ልክ ዛሬ ለአብይ እንደሚያደርጉት ሁሉ….. 

መሳሪያ ልመዝግብ ይላል በዚህ ሁሉ መሀል ካፖው ብአዴን! እኛ አማሮች ደግሞ ሁለት ጎርቫቼቭ ያለን ይመስላል:: 

ሰአቱ ረፍዷል! ጎበዝ አልቆች በቦታ ቦታ በውስጥ ለውስጥ ተሰለፍ ቶሎ:: እስኪነቃ እያሉ ማንኮራፋት አንድም ለመጥፋት ነው አሊያም አንገትን ጎንበስ አርጎ ለመገዛት ነው! 

እናም “አሁን ከማእዱ አምብሮኝ እጁን የሚያጠቅሰው አሳልፎ የሚሰጠኝ እርሱ ነው” አሁን እጁን እያጠለቀ ያለው አሳልፎ አገርህን የሚሰጠው ነው:: ቴሌኮም ተሸጠ ብለን እሪ እንቧ እንላለን ጦሱን ስላልተረዳን! ቶሎ ይህን እጅ ቆርጠን ካላሳጠርን እኛም በሰላሳ ሚሊየን ይሁን ቢሊየን እንሸጣለን:: 

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ

አማራና ኤርትራ ከሁለት ተራሮች ላይ ሆነው መሀል ወያኔን ያገኙበት አጋጣሚ!

0

አማራ-ኤርትራ 

ለኤርትራ ጉልበት ለትግሬ መዳከም ይሆን ዘንዳ አሁን ገና ኤርትራ በለስ የቀናት ይመስላል ይህንን አጋጣሚ በትክክለኛ ከቀመረችና ለተፈፃሚነቱ ከሰራች::

ከጥሊያን ፀረ- አማራ ጥላቻ የተወጋችበትን መርፌ ጥላ በጥቅም ላይ ያተኮረ ስልታዊ ጉድኝትን ባስቸኳይ ለመፍጠርና የፖለቲካ የበላይነትን ለመያዝ አማራ ጠልነትን አስወግዳ ለህዝቧና ለወደፊት እጣ ፈንታዋ መላ ማለት ትችል ዘንድ ድንቅ የሆነ ይህ የታሪክ አጋጣሚ ደጇፏ ላይ ቆሟል:: በሩን መክፈት ለራስ ነው! አማራን በመጥላት መወዳጀት የግድ ወዳጅነት እንዳልሆነ በድል ማግስት ወያኔ ሻቢያን ገልቦ ገርፎ በባዶ እጇ አጣጥቦ ያባረራት መባረር ለኤርትራዊያኑ የቅርብ ግዜ ገፅታና እውነታ ነው፥፥ ኤርትራዊያኑ ለመጀመሪያ ግዜ በኢኮኖሚ መሽመድመድን እና ድህነትን እስከ አጥንታቸው በትግሬው ወራሪ ተወግቶ በመውደቃቸው መሆኑ ፀሀይ የሞቀው ያደባባይ ምስጢር ነው:: የዛሬዎቹ ቱጃር ትግሮች የቀድሞው ኤርትራዊያንን ለመምሰል ደፋ ቀና እንደሚሉም የታወቀ ነው:: ልክ እንደ አማራው ሁሉ ይህች የበታችነት ስሜት ናት ሻቢያን እንዲክዱ ያስገደዳቸው! የነፍስ አባታቸውን ገድለው እንደ ነፍስ አባታቸው ልጆች ለመምሰል ድራማ የጀመሩት::

እና ኤርትራ አሁንም በዚህ ፀረ አማራ ዶሴ ዳዊት ደገማ ላይ ከሆነች ኤርትራ እንደ ሀገር መክሰሙን ትቀጥልበታለች፥፥ ጣሊያን የሰራውን ግንብ ሲወለውሉ ከመዋል ውጪ የኤርትራ ተራሮች ከሰል እንጂ ዩራኒየም እንደሌለው የተዋወቅን ይመስለኛል አሁን፥፥ እናም ለሁለታችንም መነሳት የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚለውን ብሂል ታሳቢ አድርገን ብሂሉንም አልፈነው ውል ያለው ጉድኝት መፍጠር ይቻላል:: ጅርመንና እስራኤል አብረ መስራት ከቻሉ እኛም ምንም ምክኒያት አይኖረንም አብሮ ላለመስራት::

ምንም እንኳ ሻቢያ አማራውን ጠምዳ ይዛው ወያኔን አምጣ ብትወልድም አንድ ነገር ግን እናውቃለን የማንነት ቀውስ እስኪሰጣት ድረስ የትግሬውን ክህደት ታሪክ ተከስቶባታል፥፥ “አማራ በጣልህ” እያለች ስታስፈራራውና በዚህ ማስፈራሪያ ያደራጀችው ህዝቧ መጣልህ ባልተባለ ባልተገመተው ወያኔ ተመጥቶበት የኤርትራን ህልውና ፈተና ውስጥ ወድቆ ለዛሬው አጣብቂኝ ውስጥ መግባት ብቸኛው ምክኒያት ነው፥፥ በትግሬውና ኤርትራው በተነሳ ሹክቻ መሀል አማራው መሀል ገብቶ ሀይ ብሏል:: በነዚህ ሁለት አማራ ጠል ጠብ መኃል ገብቶ ገላግሎ የኤርትራዊያኑን ከአገር መባረር እራሱን መሀል አስገብቶ ለመታደግ ብዙ ዋጋ የከፈለበት ነው፥፥ አማራ ታማኝ መሆኑን ለኤርትራዊያኑም ጠላት አለመሆኑን በታሪክ አስመዝግቧል:: ኤርትራዊያኑ ከሀገራችን ሀብት ንብረታቸው ተዘርፎ ሲባረሩ አማራ ልጆቻቸውን በማደጎ ወስዶ በማሳደግና በጠባቂነት በመያዝ ብሎም ንብረታቸውን ጠባቂም በመሆን መከራከሩን ታሪክ መዝግቧል፥፥ አማራ ወዳጅ መሆኑን አስመስክሯል፥፥ አማራ በጅምላ ህዝብን ፈራጅ እንዳልሆነም አሳይቷል፥፥ አማራ ምጡቅ ረቂቅነቱን ሰው የጠፋ ቀን ሰው ሆኖ አስመስክሯል:: ኤርትራዊያኑ ኮዳ ይዘው በባስ ሲጫኑ “አማራ ነው እንጂ ወዳጅ አብሮ ከበላ የማይክድ” እያሉ በእንባ ተራጭተው የአውቶቢሶች ሞተር ተነስቶ ከአይነስኪጠፋ አማራው ቁሞ እያየ በእንባ እንደሸኛቸው ኤርትራዊያኑ እራሳቸው ህያዋን ምስክሮች ናቸው፥፥

እናም ዛሬ የግምቦት -1 መፍረስና በODF መካድ ለኤርትራ ትልቅ መልእክት ይሰዳል፥፥ ኤርትራ በአካባቢው ላይ ሚና እየተጫወቱ መቀጠል ካሻት አሁን ባስቸኳይ ማድረግ ያለባት አንዱና ዋናው ግምቦት -1 ከአገሯ ማባረርና ግልፅ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት ሲሆን ኦሮሞው ሀይል ከድቶ አገር ቤት መግባትና በድብብቆሽ ወደ ስልጣን መምጣት ከኤርትራዊያኑ እጣ ፈንታ አንፃር ፋይዳው ምንም ከመሆን ባሻገር ኤርትራን ሚና እንዳትጫወትና ከጥቅም ውጭ ስለሚያደርጋት በቶሎ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚለው ህሳቤ አንድ ትልቅ እርምጃን ደፋር በመራመጅ ከጥላቻው በላይ የአማራውንና የኤርትራውን ጉድኝት ማጥበቅ ግድ ይላታል፥፥ ይህ ባይሆን ኤርትራ በገዛ እጇ የመቃብሯን ጉድጓድ ትቆፍራለች:: እንደ ህዝብም እንደ አገር ትከስማለች:: የመክሰሙን ጉዞም ታፋጥናለች::

አዲስ ህይወት ይዞ ለዘመናት ለመሮጥ በስልጠና ላይ ያለው ፈርጣማው የአማራን ፖለቲካ ማጎልበት ለኤርትራ ለራሷ ህልውና ይበጃታል፥፥ ግምቦቴን ማባረሩዋን አውጃ ኤርትራ ያሉ አማራ ንቅናቄ ግንባርን በሰፊው በተጨባጭ ድጋፍ ለመስጠት ውሳኔ አድርጋ ይህን ይፋ በማድረግ የዘመናት ቁርሾን በዚህ ልትክስ ሲያስችላታል! ይህ የካሳ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ግን ከሁሉም በበለጠ አዋጭ የፖለቲካ ካርታ ነው፥፥ ወፍራም ካርታ! ጆከሩን ከአማራው ሀይል ጋር ይዛ በቀኝም በግራ መብላት ይችላሉ ሁለቱም ጎራዎች! እንዴት? አማራውን በዚህ መልክ ለመርዳት ኤርትራ ዝግጁ ከሆነች ከሁሉ በላይ በአካባቢው ላይ ፖለቲካዊ ሚና ተጫዋችነቷ ይቀጥላል:: ይህ ቅንጅት አማራው በድሉ ማግስት ለኤርትራ እነ ጤፍ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦት እንደሚያደርግና ኤርትራም በምላሽ የወደብ ግልጋሎትን ለአማራው በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ማጠናከር ይቻላል፥፥ ዛሬ አገራቸው ለጉብኝት የሚሄዱ ኤርትራዊያን ምግብ እንጂ ልብስ እንዳይጭኑ የምናውቀው ነው ግን ይህንን ስምምነት በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል:: እነኝህ ሁለቱ ህዝቦች ከሌላው በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ማህበረሰቦች በተለየ የሚያመሳስላቸው ስነልቦና ባለቤት ናቸው ያውም ሁለቱም በራሳቸው የሚኮሩ ህዝቦች መሆናቸው ነው:: የትግሬውን አይነት ርካሽ ፖለቲካ በዚሁ በአማራውና በኤርትራዊያኑ ኩራት ለበስ ስነልቦና የተነሳ ሲበለጡበት ኖረዋል:: ወደፊት ግን በዚህ መልክ መቀጠል የለበትም ብዬ አምናለሁ:: ኩራት እራቱ ብንሆንም እራት ግቆመን መጋቢዎች መሆናችን መቀጠል የለበትም አይቀጥልምም!

ስለሆነም ኤርትራ ቀጣይ ሚና ተጫዋችነትና አገራዊ ህልውናዋ ብሎም ለአማራው ህልውና ቀጣይነት የሁለቱ አገራት ህዝቦች የወደፊት እጣ ፈንታ በዚህ ተሳስሯል። ይህንን ስልን ግን የአማራው ብሄርተኝነት ኤርትራ ባለ ጦር ይደገፋል ለማለት ሳይሆን ነገር ግን መሀላችን ላይ ያለ እኔ ብቻ የሚል እብሪተኛ ጠላት ወያኔን ለመክበብ ያመቻልና ነው። ለመክበብ ነው አይዞን። አማራ ብሄርተኝነት መሬት እንደያዘ በአገር ቤት ወስጥ ለውስጥ በህቡዕ መንቀሳቀሱን ይቀጥላል። ስር ነቀል ለውጥ በአፍሪቃ ቀንድ ላይ ለማምጣትና ተጨባጭ መረጋጋትን በመልካም ጉድኝነትና የንግድ፣ የልውውጥ ትምህርት ወዘተን በማዳበር ለአካባቢው ዋስትናን መስጠት ይቻላል፤ ይህንን ዋስትና ማምጣት የሚችሉት ሁለት ትልቅ ሀይሎች አማራውና ኤርትራው አብረው መስራት ከቻሉ ነው። የሁለቱ አብሮ መስራት ጠላትን ቀለበት ከመክተቱ ባሻገር ዘለቄታዊ የጥቅም ትስስር ስለሚኖር በህልናቸውና የወደፊት እጣ ፈንታቸው መቆራኘት የተነሳ የሚያስተማምን ለዘመናት የሚደጋገፍ መጣመርን መፍጠር ይቻላል። ከአማራው መጎዳኘት ይበልጡን ለአርትራዊያኑ የሚረዳበት ዋና ውና ብዙ ሊጠቀሱ የሚችሉ ጉድኝነት መካከል አማራው በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብልና የእህል አቅራቦት ዋናው በመሆኑ ኤርትራ የዚህ ምርት ተጠቃሚነትን በተመጣጣኝ ዋጋ ስታገኝ አማራ ምርቱን ወደ ሌላ አገራት ለሸያጭ የሚያወጣበት መንገድና አሱም የሚያስፈልጉትን ቁሶች የሚያገኝበት ሁኔታ ይመቻቻል ማለት ነው። የስራንም እድል ከፋች ነው:: ሁለቱም በአያሌው ይጠቃቀማሉ ማለት ነው።

ይሄ ወርቅ የሆነ ታሪካዊ አጋጣሚ ነውና ሁለቱም አገራት (ሕዝቦች) በቶሎ መክሮ አካባቢውን ከአናሳ ጠባብ የትግሬው ቡድን ውጭ ማድረግ ግድ ይላል። የኦሮሞ መጎልበት ኤርትራን በጂኦ ፖለቲክሱ ከሚና ውጭ ተጽእኖ ፈጣሪነትን ይነፍጋል። ለአማራው የኦሮሞ ብሄርተኝነት መጎልበት ጥፋት ለመሆኑ አርባ ጉጉ ጀምሮ አስካሁን እስከ ትናንትናው ከናዝሬት ከገዛ ቀዬው መባረር ያለውን ጭፍጨፋ እያየነው ያለ ፋሺስታዊ ድርጊት ነው። የህልውናችን ቀጣይነት ችግር ውስጥ መግባት ያስተሳስረናል!

ይህ ጉዳይ ዛሬ ነገ ሳይባል በቶሎ በሁለቱም ህዝቦች ጥምር ቅንጅት ሊተገበር ይገባል።

ድል አማራ ህዝብ!

መደራጀት ማለት ምን ማለት ነው 101

0

አማራ ሆይ መደራጀት ማለት ምን ማለት ነው? ምን ስንሆን ነው ተደራጀን የሚባለው? እነኝህ ጥያቄዎችን ስንመልስ የመደራጀት ትርጉሙ ይፈታልንና በቀላል ተግባራዊ ይሆናል:: መደራጀት ሂደት ነው:: ስልት ያለው ሂደት! መደራጀት እንዳያችሁት ላለፈው አራት አመት እንደምናደርገው ሁሉ መጀመሪያ ዋናው የማንቃት ስራ/ዘመቻ ነው እያደረግን ያለነው:: ህዝብ ሲነቃ ደግሞ ሰብሰብ ይላል ሊያወጋ:: በሩን ጥርም አድርጎ ዘግቶ:: ይመክራል:: ከዛም ጎበዝ አለቃውን ይሾማል:: ከዛ ከጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋ፣ቤተ አማራ (ወሎ) ምስጥራዊ ድር ያደራል:: ዋሻ ዋሻውን በአራቱም ክፍላተ አገራት ጠግጥጎ ይይዛል:: በዱር ይማራል፣ ይመክራል:: በከተማ ያለውም በየስፍራው ሁለት ሶስት እየሆነ ይመክራል:: ማህበራዊ ድህረ ገፆችንምይጠቀማል:: ከውስጥ እስከ ውጭ፣ ከዱር እስከ ዳያፕራው ድር ይምጋል:: ይያያዛል:: ሚዲያ ተጠቅሞ ሰፊ ማንቃት ስራውን ሌት ተቀን ሳይል ይቀጥላል:: በማንቃት ስራ ላይ አንድ አላማ ያስይዛል:: ታሰረ ተፈታ፣ ተያዘ ተገደለ፣ ልማቱ ቀጨጨ ገለመሌው ውስጥ ሳይገባ ስለሌላው ለማውራት ምንም ግዜ ሳይሰጥ እራስ ተኮር ትግል ያጧጡፋል:: ድሩን ያጠብቃል::

ትግሉን ሀ ብሎ ሲጀምር ከመሀሉ ያለውን ቅጥረኛ፣ ሎሌ፣ ሆድ አደር ባንዳ ባዳውን በማጥራት ስራውን ይጀምራል:: ውስጡን ሲያጠራ ከዱር ሆኖ ወጣቶችን የሚያሰለጥነው በፖለቲካም የሚቃኘው ሀይል በውድም በግድ ወደ ዱር አማራዊውን ያስገባል:: ወጣቱን ታዳጊ የአገር መሪ እና ጠባቂ ለማድረግ በፖለቲካ ያነቃል:: በአጭርና በረጅም ግዜ ያለውን አላማ በደንባድርጎ ያስጨብጣል::

አሁን ልጇ ዱር ያለ እናትም ሳትወድ በግድ ትነቃለች በአማራነቷልጇ ማንነቱን ሊያድን ሸፍቷልና:: ፀሎቷ ሁሉ “አማራን ነፃ አውጣልኝ” “ለጆቼ ድል ስጥልኝ” የሚል ይሆናል ማለት ነው:: ከሰማይም ከምድርም ሀይል ተቀናጀ ማለት ነው:: አባትም መሳሪያ ደብቆ ያስቀምጣል ይወለውላል ልጁ ሀይ ሲል ከዱር እሱ ከከተማ ሊያግዝ:: አ የትኛዋም አማራ እናት ማእከላዊው መንግስት ወርቅ ቢያፈስላት ልቧ ልጇ ያለበት ዱር ይቀራል:: ድጋፍ ተገኘ ማለት ነው:: እህትም ወድሟ ሲናፍቃት ዱር ትከተላለች:: ጓደኛዋ ሲዘምት ፍቅርም ያስገድዳል እንድትከተለው:: እሷም ብን ብላ ዱር:: ወንድሞችን ከመመገብ እስከ ጥበባዊ ምክር ብሎም በሰልፍ እስከማገዝ ትልቅ እገዛ ታደርጋለች ማለት ነው::

ከዛ አስተባባሪው ድምፅ ግፋ ሲል ጥቃት ከያቅጣጫው በመሰንዘር አማራዊ ምድርን ነፃ ለማውጣት በሽፍታ ስልት እያጠቁ ዋና ዋና ተቋማትና አውታሮች ላይ አደጋ በመጣል በመንግስት ወንበር ያለውን ወንበሩን ለማስለቀቅ አስገዳጅ ሆኖ ይታገላል:: እያለ ሁሉም አማራ ለአአንድ አማራ በሚል ይሰለፋል:: ትግሉም በድል ይጠናቀቃል:: አማራዊ አስተዳር አዋቅሮ አማራ ለአማራ በአማራ የሚለውን አሰራር በጊዮናዊ ሁሉን አቀፍነት የአማራ ብሄርተኝነት ባዲራውን ከፍ አድርጎ ይተክላል::

ትግል ብሎ ሰላም፣ ትግል ብሎ አዳራሽ የለም:: ታግሎ አሸንፎ ነው አዳራሽ የሚገባው!

ትግል ብሎ ዱር፣ ትግል ብሎ ማንቃት፣ ትግል ብሎ ብረት ነው ያለው::

ይቀጥላል…….

ድንበር የለሹ ግብይት፥ ቪዛ የለሹ ጉብኝት

1

ትልቁ ቅዠት የትግሬ ህዝብ እንዲያምነው የተደረገው ደርግን ገርስሰው ስልጣን በመጋደል እንዳገኙ እንዲያምኑ መደረጋቸው ነው:: ስልጣን በውጭ ሀይሎች ተሰጥቶዋቸው እንደተቆናጠጡትና ሰጪው በቃ ሲል ስልጣን ላይ ለመቆየት ለአንድ ቀን ምንም አይነት ሀይል ብቃት እንደሌላቸው የሚያወቁ አይመስልም::

እነሱ ብቻ ሳይሆኑ በዚህ ቅዠት ዋዣቂ ብዙኃኑም ጭምር ይህንን የተረዳና የተገነዘበ አይመስልም:: ስልጣን በውጭ ሀይሎች ድጋፍ መከዳ ካደረገ ዘመን የለውም::

ሀይለስላሴ በእንግሊዝ ምርኩዝ፥ ደርግ በራሻያ መከዳነት፥ ወያኔ በአሜሪካን ከዘራነት ስልጣን ላይ እንደቆዩ ማወቅ እየተካኃደ ያለውን የሰሞኑን ድራማ ለመከታተልና ጉዞ ወዴት እያመራ እንዳለ ለመረዳት ይበጀናል::

አሜሪካኖች ጵወዛ ላይ ናቸው:: በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ እንዲህ አይነት በፍጥነት ተለዋዋጭ ነገሮች ሲበዙ በስልጣን ግርግር በ60ዎቹ ብሎም በ83 እንደሆነው ሁሉ ዛሬም ዋና የሆኑና የአገራችንን የወደፊት ጉዞ አቅጣጫ ቀያሽና ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ይከናወናሉ:: አሁን አብይን በአክተርነት አወዛዋዡ የውጪው የማይታዩ እጆች የከፋው ለመጨረሻው መጨረሻ እያሰናዳን ያለ ነው፤ ይሄውም ኢትዮጵያን denationalize የማድረግ ሂደት privatisation በሚል ስልት ታክኮ መጥቷል::

ካፒታሊስት አይደለም፥ ሊብራል ኢኮኖሚም አይደለም፥ ሶሻሊዝምም አይደለም፥ ናሽናሊዝምም አይደለም፥ ፌደራሊዝምም አይሆንም …. ይህ ወገኖች ግሎባሊዝም ነው:: ድንበር የለሹ ግብይት፥ ቪዛ የለሹ ጉብኝት፥ ገንዘብ በአብላጫ ለያዘ ብቻ የሚከፈት በር ይሆናል:: ዲናሩን ካሳየ ናይጄሪያ ዋና ዋና ንግድ አውታሮችን እንደ real State ያሉትን ይቆጣጠራል አገርህ ላይ:: አንተ ቺስታው (በንፅፅር ነው ይህንን ስል:: ለምሳሌ የዲ ኤች ገዳ ባለቤት የነበሩ ባንድ ወቅት በምንም መልኩ በንግድ ዘርፍ ውስጥ ከነአልሙዲንና ህውሀታዊያን መፎካከር ስያቅታቸው “ድሀ እዚህች አገር ላይ እንዴት ነው የሚኖረው” እንዳሉት ያለ ችስትነት ነው የማወራው፤ ገንዘብ ያለው ችስትነት፥ ወደ ገንዘብ የለሽ ሊያሽቆለቁል ቁልቁል የተጣደ ቺስትነት) እናም real stateቱ ሲጠናቀቅ ለፈለገውና ጫን ያለ ረብጣ ላሳየው ይሰጣል:: ያ ደግሞ ጋናዊ ወይንም አረብ ይሆን ይሆናል:: እንደነኒዮርክ “አዲሶቹ ከተሞች” አዲሳባ ገንዘብ ለያዘ የግዜው ሰው/ሮቦት የማንም መናኸሪያ ትሆናለች ማለት ነው:: ሲለጥቅም ኢትይዮጵያ! አንተ ኑሮው እንደ ጣፊያ ስጋ ሙቀቱ ኩምትር ሲያደርግህ ለቀህ ርቀህ ከከተማ ጎጆ ትቀልሳለህ ሪል ስቴቱና መንገዱ በመስፋት መስፋፋት ወዳለህበት እስኪደርስ:: የዶሮ እንቅልፍ ይሆናል እንቅልፍ:: ያለቪዛ ሰርቆም ይሁን ገሎ ብር የያዘ ከተማህን ለመጎብኘት ይመጣል:: ይህ ምን ማለት ነው? ሲብራራ እነሲንጋፖርን በsex destination እናስከነዳለን ማለት ነው:: ያገርህ ሴት ልጅ ባይን ቂጥ ታይሀለች ያኔ:: ድቅልቅሎች የወደፊቷ ”cosmopolitan” አዲስ አበቤዎች ልጆች ይሆናሉ ያኔ ጉሮ ወሸባዬህ ወደ ጓሮ መዋያዬ ይሆናል የአገርህ ዜማ!

ዛሬ ምንም ባልተለወጠ ለውጥ ሰልፍ መሰለፍ ስለቻልክና አለአግባብ የታሰሩ ሰዎች ስለተፈቱ ይህንን ከለውጥ ቆጥረህ ልደመር ያልክ ካልኩሌሽን ማሽኑ በደንብ ሊደምርህ ተዘጋጅቷል:: አንተ በዜሮ ቁጥርነት ብቻ ነው የምታገለግለው subservient ሞድ ላይ ተለውጠህ you’ll function at a servitude level, nothing more nothing less.

አንተ የምትተኛ ንቃ! አለም አንድ መንደር ነች እያልክ ስትለፍፍ የቆጡን ልታወርድ ስትንጠራራ የብብትህ እንዳያመልጥህ! ንቃና ይህንን አለም ባንድ እንዝርት ለማሾር ለሚመጣው ስርአት እንቅፋት አቁም! እንቅፋት ሁን! “የእንቅፋት ድንጋይን በፂሆን አኖራለሁ” እንደሚል ቃሉ ማስቆም ባትችል እንኳ እንቅፋት ሁንበት- እምብየው በል!

0

Tonight, in the mid hour of the night, we are not entering a New Year.

It is bizarre that the European calendar set up at midnight hour for the day to change. What is the reason for it? According to scripture and the ancient calendar worldwide (biblical calendar), the day is set to begin when the sun rises. The sun is there to indicate days, the moon for months, the stars for years. “And God said, Let there be lights in the firmament of the heaven to divide the day from the night; and let them be for signs, and seasons, and days, and years:” Gen 1:14 The day has 12 hours of daylight and 12 night hours.

So why did sneaky Freemasonry science alludes for the day to change in the middle of the night while there is no reason or indication from the celestial bodies of the heavens? Why do we change the year tonight? There is no change of season taking place. The year changes when the season changes, and as far as we are concerned, there no season-changing going on. It would make sense if we change the year in April since the season changes then and the sun approaches in the near window of the installation in the heavens. We are in the middle of the dark winter, yet we are changing the year; we are in the mid hour of the day, yet we change the day?! 🤔

“For, lo, the winter is past, the rain is over and gone;

The flowers appear on the earth; the time of the singing of birds is come, and the voice of the turtle is heard in our land;

The fig tree putteth forth her green figs, and the vines with the tender grape give a good smell. Arise, my love, my fair one, and come away.” Songs of Solomon 2:11-13

The hour of the ruler of this world is the darkness, and that’s precisely why his children chose the night hour and the dark winter.

“Now Shall the Ruler of This World Be Driven Out”: John 12:20-36

The devil knows that his time is running out and the children of the darkness are at work falsifying pandemic and vaccine, death, and economic stress to bring creation under the feet of the antichrist. There will be time no more to the darkness. Our savior will soon appear, and we will witness the ruler of this world cast out forever, along with his pseudoscience!

Lydia Zewdu

የማይቀርበት መንገድ

0

አርባ ቀናት ሆኑ እንደዋዛ… አርባ እረፍት የሌላቸው ቀናት በሃሳብ የሚያባዝኑ:: የቁጭት ምነው እንዲህና እንዲያ ቢሆን የምልበት ብዙ መወትወት ማልቀስ ማዘን መቆዘም ደሞ ለመርሳት መሞከር…. ግን ከሰውም አለ የማይረሳ ሰው:: ስፈልግ እንደጓደኛ የምታማክር ሲያሻ እናት የምትሆን ሲላት እንደካህን ሌቱን ቆማ ብርቅባት እንኳ ስልክ አቃጭላ የምትፀልይ ስታገኘኝ ስስት የምሆንባት ፈገግ እያለች ብቻ ዝም ብላ የምታየኝ …. ልዮ ስሜት የምትሰጥ! እንደ እንቁ ተንከባክባ የከበረ ስሜት እንዲኖረኝ ስለራሴ የምታደርግ አስተዋይ ….እርሷ እስካለች ድረስ ፀሃይ ብትጠልቅ ፈገግታዋ ብቻ ጉሙን ይገፍልኛል የምላት ከእናት በላይ የሆነች እናት …. ምጡቅ አእምሮዋ ስታስተምር ካፏ መሬት ጠብ ሳይሉ ነበር ምክሮቿም ሆኑ ምሁራዊ አመክንዮዋ! ስትገስፅ አቅንታ ልታሳድግ ሲላት ደሞ ጓደኛ ሆና ሚስጥር የምትካፈል ሁለ ነገሬ ነበረች እናቴ ግን ደሞ የማይቀርበት መንገድ አለ:: ማስቀረት አልተቻለም! አንጀቷ እንዴት እንደቻለ እንጃ የልጆቿ ነገር የማይሆንላት ሰው ነበረችና:: ሁሉ ሰው በደግነቷ ያውቃታል:: ደግነት መጠሪያ ስሟ ነበር:: ምን ያደርጋል ቀን ሲደርስ ደግነትም አብሮ ሄዷል:: ቢከፋኝም ቢደላኝ እንግዲህ ብቻዬን ነኝ:: እናቴ የኔ ስስት ሁሌም በልቤ መቼም ላትወጪ ትኖሪያለሽ:: ወደ ምትወጂው ጌታሽ ወደ ተስፋው ክብር በክብር እንደተቀበልሽ አውቃለሁ:. አገልግለሽዋል በቃሉ ታምነሽ ኖረሻል:: ሩጫሽን ጨርሰሻል:: የድልን አክሊል ከእርሱ ከታማኙ ትቀበይ ዘንድ አለሽ! መሪር ብትሆንም ሃዘኔ ግን የሞት መውጊያ የተሰበረልሽ መሆኑን ሳስብ እፅናናለሁ:: በጌታ አንቀላፍተሻል እንጂ ሞት እንዳይዝሽ ያው መንፈስ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሳው በአንቺ ውስጥ አለና ጌታን በምፅ አቱ ቀድመሽ እንደምትገናኚው አውቃለሁ:: በአብርሃም “አብርሃም አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረት” በተባለ የምነት አባት ፈለግ ተከታይ ነሽና በአብርሃም እቅፍ እስከ ጌታ ቀን ትጠበቂ ዘንድ እንዳለሽ አውቃለሁና ልቤን በዚያ አፅናናለሁ:: ብዙ ሃሳብ ነበረን ብዙ እቅድ ብዙ ምኞትም ግን ጌታ የወደደው ሆኗል:: እግዚአብሄር ሰጠ እግዚአብሄር ነሳ ክብር ሁሉ ለሰምስይ ምድር ፈጣሪ ለነፍስ ሁሉ ጌታ ይሁን!! በከፍታም ሆነ በዝቅታ በሃዘንም ሆነ በደስታ ምስጋ. አይጓደልበት! እዚህ ለቅሶ ተብሎ ስናለቅስ በዚያ ደግሞ ሰርግ ነበር ወደ አባትሽ እቅፍ ስትገቢ… ሁለት ነገር በአንድ ግዜ ሆኗል:: ረቂቅ ስራው አይመረመርም! በአካልም በስልም ተገኝታችሁ መላው ቤተሰቧን ላፅናናችሁ ሁሉ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ!

The Only-Begotten Son is Nobody’s Brother.

0

The apostate church teaches that we are sons of God just as Jesus is and that we are made equal; this is utterly wrong! Heretics claim that Jesus is not the only Son of God as we are too- how erroneous and how we stoop so low in our teaching is dumbfounding.

Let this be clear to us that Jesus Christ [Yeshua Hamasciach] is the Son of God in three distinct ways.

1] Jesus is the Son of God in essence, eternity past

2] Jesus is the Son of God, born 2000 years ago in Bethlehem Judea God reincarnated.

3] Jesus is declared to be the Son of God by the resurrection from the dead.

Jesus is the only begotten Son from eternity, and He is nobody’s brother in that sense.

The man who was born from flesh 2000 years ago, that’s our brother for he partook from our nature.

The man born in the flesh is our brother, not the Son of God from eternity.

The ”only begotten Son” is translated from the Greek word Monogenes. The word Monogenes has two primary definitions, “pertaining to being the only one of its kind within a specific relationship” and “about being the only one of its kind or class, unique in kind” Jesus the only begotten Son of Holy Living God from eternity is one of a kind. Jesus is a Son of God from eternity, not by becoming. He is the second person of Trinity.

We, on the other hand, are made to be sons of God. There is a big difference between being and becoming. Let us be thankful for being made His sons and stop equaling ourselves to Christ.

Reference:-

Romans 1:4
And declared to be the Son of God with power, according to the spirit of holiness, by the resurrection from the dead

Isaiah 9:6
For a child will be born to us, a son will be given to us; And the government will rest on His shoulders; And His name will be called Wonderful Counselor, Mighty God,
Eternal Father, Prince of Peace.

Colossians 1:17
He is before all things, and in Him all things hold together.

1 John 1:1
What was from the beginning, what we have heard, what we have seen with our eyes, what we have looked at and touched with our hands, concerning the Word of Life—

Revelation 1:17
When I saw Him, I fell at His feet like a dead man. And He placed His right hand on me, saying, “Do not be afraid; I am the first and the last,

Revelation 1:8
“I am the Alpha and the Omega,” says the Lord God, “who is and who was and who is to come, the Almighty.”

Hebrews 7:3
Without father, without mother, without genealogy, having neither beginning of days nor end of life, but made like the Son of God, he remains a priest perpetually.

Revelation 1:18
and the living One; and I was dead, and behold, I am alive forevermore, and I have the keys of death and of Hades.

Hebrews 7:16
who has become such not on the basis of a law of physical requirement, but according to the power of an indestructible life.

ስሁቷና ኮብላይዋ ከዳተኛይቱ ባቢሎናዊት ቤተ ክርስቲያን ጌታችን የሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስታጣምም ጌታችን አንድያ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑ እኛ በዳግም መወለድ ከተቸርነው ልጅነት በምንም አይበልጥም ስትልና የክርስቶስ በዘላለም ውስጥ የወልድ ህላዌነቱን ልትተካከል ሽታ ምእመኗን በአሳቻ ትምህርት እየነፋፋች ለትእቢትና ለይገባናል ምፀት ተገብዛ ታጋብዛለች! ምን ያለ ስሁትና ድፍረት ጭካኔ የተሞላበት ትምህርት ነው? ባቢሎናዊቷ ተራማጅነትን አንጋቢ የእግዚአብሄርን ቃል ልታሻሽል ከዘመን እኩል ይራመድ ብላ የእግዚአብሄርን ቃል ዘመን ተሻጋሪነቱን ዘንግታ ዘቅጣ ዘቅጣ የሲኦል ወለል ላይ ትንደባለላለች ያለችው! ፂሆን ሆይ ያንገትሽን እስራት ፍቺ! አቧራሽን አራግፊ ስለስሙ ስትይ ፀጋውን ረግጠሽ የእውነትንም መንፈስ አታክፋፊ ከወዴት እንደወቅሽ አስቢ! ንስኃ ግቢ! ሰባኪው ሆይ ተመለስ ከስሁት ትምህርትህ ቶሎ ሳይመሽብህ!

ይህ ይረገጥልን! ጌታችን እየሱስ በሶስት መንገድ የእግዚአብሄር ልጅ ተብሏል::

1) በዘላለም እስከዘላለም ቁጥር በሌለው አመታቶቹ በማንነቱ በእግዚአብሄር ልጅነት ህላዌነት ከስላሴ አንዱ በመሆን ወልድ ተብሎ መኖሩ

2) ጌታችንና መድኃኒታችን የሱስ ክርስቶስ በስጋ የእኛን ዘር በመያዝ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ሆኖ የዛሬ ሁለት ሺህ አመት በይሁዳ ቤተልሄም ከእግዚአብሄር በመወለድ ልጅነት

3) ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳት በኃይል የእግዚአብሄር ልጅነት

የጌታችንና የመድኃኒታችን የክርስቶስ የሱስን ማንነት ለመረዳት እነኝህን የነገረ ክርስቶስ ሃቆች በጥልቅ መረዳት ግድ ነው!

ጌታችን የሱስ ክርስቶስ በዘላለም ቁጥር በሌለው አመታቱ እና ህላዌነቱ ውስጥ ብቸኛ አንድያ የእግዚአብሄር ልጅነቱ በዚህ ረገድ የማናችንም ወንድም አይደለም::

በይሁዳ ቤተልሄም በስጋ ከመላእክት ዘር ሳይሆን ከሰው ዘር በድንግልና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከብፅእት ማሪያም መወለዱን ለምናምን ደግሞ ወንድምነቱ በዚህ አኳያ ነው:: የእኛ ልጅነት ዳግም ከመንፈሱ በመወለድ የሚገኝ ነው:: የእርሱ ልጅነት ግን በድንግልና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መወለድ በፊትም ወልድነት ከስላሴ አንዱነት ባህሪዮ ነው:: የማይለወጥ በመደረግ ሳይሆን በመሆን ወልድ ነው:: እኛ ደግሞ በእርሱ በማመንና ዳግም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከእርሱ በመወለድ ነው የእግዚአብሄር ልጅነት ያገኘነው:: የእኛ ልጅነት በመደረግ ሲሆን የእርሱ በመሆን ነው::

አንድያ የእግዚአብሄር ልጅ የሚለውን የግሪኩ ቃል ሞኖጊኔየስ ሲለው ትርጓሜውም በአይነቱ በማንነቱ ኃምሳያ የሌለ. ብርቅዬ ብቸኛ የሚል ሲሆን በተጨማሪም ከአብ ጋራ ባለው ግንኙነትም ማለት አንድነትና መተካከል ብቸኛ ብርቅዬ የሚመስለው የሌለ ማለት ሲሆን የስላሴ አንድነቱን [Godhead] አምላክነት ልጅነቱንም የያዘ ብቸኛ አንዲያ ልጁነቱን ይገልጣል::

እናም ከዳተኛይቱና ስህቷ ቤተክርስቲያን ም እመኗን በዚህ ክዳትና መውጫ የሌለው ጥፋት እንዳትከት ትምህርቷን ብታስተካክል በቶሎ ይበጃል:: እኛ ልጅነትን በፀጋው በመወለድ ያገኘን በእግዚአብሄር ፍቅር ድንቅ ስጦታ ልጁን በማቅርብ ከእኛ የታረቀበትን ይህንን ድንቅ ማዳን ስለተቸርን በትህትናና በመፍራት መዳናችንን ልንፈፅም እንጂ እራሳችንን እንደሚገባን ቆጥረን መተካከል ሽተን ከማንተካከለው ልንቃማ እራሳችንን በአጉል ውሸት ሞልተን የክርስቶስ ተፃራሪ ሆነን እንዳንገኝ ምሳሌውን ፍለጋውን የተወልንን ክርስቶስ የሱስን ፍለጋ እንከተል:: እርሱ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር መተካከልን እንደመቀማት አልቆጠረም ይልቁን እራሱን ባዶ አድርጎ በምስሉ የባሪያን መልክ ሆኖ ተገኘ እንጂ:: እኛ ደግሞ በባሪያ መልክ ያለን የልጁን መልክ ልንይዝ ስንጠራ ጭራሽ ነን በሚል ድፍረት ልባችን እየኮራብን እራሳችንን በቦዶ ጉራ ሞልተን የልጁን መልክ ልንይዝ ያለውን ጥሪ ችላ እያልን የራሳችንን መልክ አናግዝፍ! አምላክነትን ስንሻ በልቡ ኩራት ተገኝቶበታልና በአመድ ላይ እንደተጣለ ከእግዚአብሄር ገነት እንደተባረረ እሳት ከውስጡ እንዳወጣበት እንደ ዲያቢሎስ በኩራትና በይገባኛል መንፈስ አንነፋፋ!

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችን ጋር ይሁን።

ሊዲያ ዘውዱ

Its not about Our Rights, its About His Rightousness

0

Today’s Church does way too much motivational talking. It’s deafening; the church doesn’t echo what the spirit is saying. Teachings are increasingly irrelevant to the core idea of the scripture. I don’t hear church leaders preaching about sin these days. All I hear is that ”do good, be good, feel good” crap over and over again.

The devil was the first motivational speaker! Yes, he was the first to sensationalize the supreme law of our Abba Father. He fascinated Eve, suggesting the same false gospel that he sneaks into church houses today, ”you are god.” Baal Cult.

I mean, think about it, Eve has everything she can ever ask for under the sun, but the devil somehow managed to beguile her, making her feel she is short of something. Something she is not aware of- this is his duping tactic. The devil plays with our mind by reasoning. What’s interesting here is that the devil didn’t bring a whole new set of teaching. Instead, he twisted the same commandment that Eve was aware of. Just like what we nowadays do, she began to clowning around for a new revelation, a new ”manifestation” of the word by digging into this seductive pedagogy.

Instead of meditating on the word day and night as informed, Eva was all out for a new exploration of her own, which stumbled her at the valley of human RIGHT AND EQUALITY, forgetting altogether that she was virtuous, righteous and that she lacks absolutely nothing. Then satan started to add fuel to the fire by elevating the quest to a morality issue. He conned her into thinking that she can guide her destiny [her right] without the need to submit to God; the privilege of eternity is her very nature, and she is a goddess [not a created being]. The devil knows the thought of Equality, Right, and Morality entices the natural man. Morality is something that man himself sets according to his understanding. It makes the natural man feel good and in control. It’s hard for the natural man to be without this feeling of control that he thinks he has in this life. Therefore, we see throughout human history; man boasting of how far he has come in this excursion of life being a mini-god who is in charge of directing his fate and the world without a need of his creator. While at the same time, a feeble virus brings a man and his fallen world as a whole to its knees. Though our Bible warns us, clinging to our understanding is futile, we are haunted by that inexplicable desire that our mind loves to feed on- power. Knowingly or unknowingly, we race with this feeling of wanting to be in charge of our destiny while, in reality, we are incapable when the situation presents itself.

Because of this craving, the Church often run with half-truths of the scripture to come upon a new manifestation. For instance, the verse the preacher frequently utters to claim that we are little gods,” Ye are gods, all of you are children of the Most High.” this verse is completely isolated from the context to coax the congregation into the blasphemous chatter….. The ” you are little gods” teacher often creates a pretext for the impiety he teaches, while contextually, the very next verse speaks of the precise nature of our life in this existence…. ” But ye shall die like men and fall…..”

It is customary to today’s church to bring ancient mythology dressing it up with the word of God to give it a Christian spin; ”Man is spirit,” man is a little god” prosperity gospel psycho-blab, Dominionism, the Kingdom Now erroneous teaching, etc.

So Ms. Eve was stimulated with all the inquisition and the new philosophy that the devil was ”revealing, ” …..she must have felt powerful and in a position to delineate her own destiny without the need of submission of God.

Just like that, Eve got into an institutionalized belief system as suppose to direct relationship with her creator. The devil delivered the first sermon, titled Man Is God, ”Ye shall be like God”……. Eve was reluctant, fearful, and rigid at first. Satan must have hummed her with buzz words like ”be positive, don’t be religious, a breakthrough is at hand, name it, claim it, grab and blab it”……. then abruptly, the tree that she walks by every day becomes that desirable and good to eat. The devil’s husky voice indisputably lured her, clouding her perspective. Before she knows it, eve was trapped and enticed by the beauty of the fruit she is forbidden to eat. This is precisely why the Bible says to not give a chance to the devils’ doctrine. He uses the same book! He has mastered how to manipulate and use it against us.

The first ground for Eve to lose in the spiritual battlefield was when she exaggerated the commandment of God ”tge day you eat or TOUCH the tree you will die”…Why did she bother to inflate the command? God didn’t say the day you touch of it, but you eat of it. That’s what got her in the web of deceit. It feels she has an unspoken detest for the commandment.

”But of the tree of the knowledge of good and evil, thou shalt not eat of it: for in the day that thou eatest thereof thou shalt surely die.” Genesis 2:17

Often the devil’s advice appeals to the fallen humanistic nature of man; it’s normal to take God out of the equation; he knows it. But look where it led the whole creation.

We are approaching the tribulation period. Folks, get right with the creator of your soul. Dump all the ” be good, feel good” cheap false gospel you are given. Judgment is coming! Your ”don’t be judgmental” rhetoric ain’t going to save you! We will all face His judgment seat, whether we like it or not. All tongues will profess that Jesus is Lord, and all knees will bow; it’s a matter of time. No one will stand before Him to talk about the Right, equality, and Moral of dogma when He shows up. No knee will stand firm; it will plummet. If we refuse to do it willingly now, on the day He arrives, no one can stand the heat; no knee will be strong enough to stand before him. Your religious dogma and philosophy are not going to save you either. Your faith in Him the Blessed Hope will save you! The spirit that we are born of is the one who will testify on behalf of us to salvage us from mortality.

Covid is the smokescreen; the worst is yet to come! The vaccine is a test for a bigger plan the globalist elitists are plotting. Those without the blood of the holy Lamb and those who are not sealed with the Holy Spirit will have no strength to stand against the strong delusion that’s coming. What lies ahead is worst than covid, the vaccine, etc

Get right with God today! Believe in Jesus’s righteous work. There is no other name given under this heaven, but Hamessiach Yeshua/Yesus that saves from this cyclical mortality!

Lydia zewdu.

Perpetrators Of War

0

The truth is the war is not about Tigray, Amhara, oromo, or even Ethiopia’s sovereignty! Like said from the get-go, this is a Pseudo-War. The battle seems to be about power, a fight between a baby junta vs. an old junta to consolidate political power; however, the reality is far from that. The employer of Abiy and TPLF needs this war for some serious reason. Both these parties give a jack about their people; they hold on to power as a gatekeeper for Big Brother.

The West perpetrates mass displacement, mass murder, genocide, etc., all of these events through their puppets. This war’s main agenda is depopulation and human trafficking. That’s why mass eviction was done by staged knife murder. Why? Well, think about it, the West is dependent on Africa for its survival and advancement. If there is no war in Africa and agricultural industries is to boom, where would the rest of the world be? If we produce and eat our own food, use our own resources, produce our own commodities, where would that leave the EU and the rest of the world? The answer is clear if Africa uses its resources, and we no more migrate, it would unplug the whole Western civilization’s life support, which will leave the West in a trench of poverty! This is why Africa’s prosperity is a threat to the West!

White people have been anxious about our number since Genesis! Our number threatens them. It’s an existential threat to them. Henceforth, the mass incarceration of black men in the US, endless war in Africa, slavery, human trafficking, political and economic instability are purposely triggered. Every twenty years, Africa repeats the same cycle not by coincidence but by design.

This very war we are engaged in right now is the extension of that very same notion!

”Now there arose up a new king over Egypt, which knew not Joseph And he said unto his people, Behold, the people of the children of Israel are more and mightier than we: Come on, let us deal wisely with them; lest they multiply, and it come to pass, that, when there falleth out any war, they join also unto our enemies and fight against us, and so get them up out of the land.” Genesis 1:8-11

This is an ”African” black people story, my dear! Amhara, Tigray, oromo, Konso all live together peacefully until the West and EU power emerged. First, they engaged in the war themselves by way of colonization; now, they no more want to deal with us directly; thus, they hire our own people to execute their agenda. That’s what makes it sad!

Waging war, starvation genocide is not a new phenomenon; it’s as old as the beginning of time. We Black people are not only enslaved and put to poverty, but we are stripped from our identity too. If you are to think Israel is white, shoot yourself! That’s the most significant identity theft our world has ever has seen.

This very war is about the greater Khazars Ashkenazi greater Isreal Agenda.

Lydia Zewdu.

በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አይገኝለትም!

0

ቢቢሲ ያሰፈረውን ቆንፅዬ እዚህ አስፍሬዋለሁ:: ለሃሳቤ ማጠናጠኛነት::

“Aid agencies are calling for an immediate temporary ceasefire in northern Ethiopia to allow aid to reach civilians affected by fighting.

The UN wants humanitarian corridors set up after two weeks of conflict between Ethiopia’s military and forces backing the leadership in the Tigray region.”

የምመለከታቸው ከተለያዮ አካላት ኤጀንሲዎች የሚለቀቁ ሪፖርቶች በድፍረት በሙሉ አፍ ልለው በምችለው ሁኔታ የተፈጠረው humanitarian crisis በትግራይ ብቻ እንደሆነ ነው የሚዘገበው:: Humanitarian Aid Agencyዎፕች እርዳታ ለማስገባት በትግራይም ይሁን በሱዳን እየተዘጋጁ ያሉት ለትግሬ ነው:: ይህ ትልቅ እመርታ ነው! ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ! አስከፊውን የጦርነት ገፅታ የተከሰተውን ችግር በደንብ በማራገብና አጋኖም በማሳየት በPR ረገድ በደንብ ስለሰሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከአለማት ሊፈስባት የተዘጋጀው ለትግራይ ነው:: This is a win-win for a new country that is emerging. The funds are being given in the name of ”humanitarian aid” to establish the newborn state- Tigray. Bravo!

አንተ ዝም ብለህ ሞዝቅ! Truth be told, what’s taking place in the Raya front is catastrophic and a gross humanitarian crisis that Amhara will have to deal with for years to come. Gonder Amhara is marching for Abiys war without any help from the federal government using its little resource, which will result in liquidation soon if it is not transpiring yet.

Tigray, on the other hand, is using this calamity thoughtfully. We have learned that Tigray has its own Telecom, Postal service, Electricity, and Internet services. Now in the name of a humanitarian crisis, they are getting all the dollars from left and right, while the government and some gullible warmongers are hiding Amhara humanitarian crisis to keep their narrative of ”Game Over” tagline. This war will not end by continuing the fight; it will be over by the pressure both sides get from the West to talk and resolve their issues. That’s when the war will end!

እና አንተ አማራው በጦር ላሽቀህና ተዳክመህ እንደገናም ብዙ humanitarian crisis ታቅፈህ እርዳታ ከየትም ሳታገኝ ፕሮፖጋንዳውም ካንተ በተቃራኒ ተሰርቶብህ ለሌላ ድህነትና ጥፋት መጣድ ቀጣይ ክስተት ነው:: ብትነቃ ንቃ እምቢኝ ካልክ መክራ ያነቃኃል::

አብይ በአዴፓው የህውሃት ልጅ ሹሞችን ሳይቀር በትግሬና ኦሮሞ ተወላጆች እየተካልህ ነው:: ከላይም የቆለላቸው መለስ ሆይ ብለው ያማትቡ የነበሩን ሰዎችን ነው:: በመተከል (ቤኒሻንጉል መለስ ሰራሽ ክልል) ኦነግን አስገብቶ የአባይን ግድብ ሚና ተጫዋችነትን ወደ ራሱ ሊያዞር ጥንታዊ አማራ ርስት ላይ እየተዋደቀ ይገኛል:: አንተ አያ ሆ ሆ ጨፍር- ጭፍን!

በዚህ ሰአት አማራ ሆኖ በአማራ ላይ ያንዣበበውን ጥፋትና መከራ የማያውቅም ማንም የለም አንወሻሽ! እንኳን አማራው ኮንሶው ያውቃል:: እንኳን አማራው ታንዜኒያው ያውቃል! አጉል ጆሮዬ ላይ መድፍ አፈንዱልኝ እንድነቃ አይነት የጨለማ ጉዞ ግዞተኛ ለመሆን መንደፋደፉ ቢቀር ይሻላል::

ጥንታዊነትን እንደ ፋሽን መያዝ በራሱ ኋላ ቀርነት ነው:: ጥንታዊ ታሪክ ይኖረናል እንጂ በጥንት ውስጥ ልንኖርና በጥንቱ በሬ ልናርስ አንችልም! የትዝታ ፈረስ የኋልዮሽ ሸምጣጭነት ነው ወደ ፊት ተራማጅነትን የከለከለን! የጥንቱ ህሳቤ በጥንት ግዜ የሰራ እንጂ ዛሬ ላይ የሚገዛ ሃሳብ አይደለም! እናም ሚኒሊክ ያነሱት ፕሮጄክት ዘመናቸውን የዋጀ እንጂ ዛሬን የሚዋጅ አይደለም:: እርሳቸውም ቢኖሩ እንደኔ ነው ሊሆኑ የሚችሉት:: ጦና ”እምቢኝ” ብሎ ቢቀር ጂፋርም ”የለም የለም” ቢል በቃ ወደ ራሳቸው አገር ምስረታ ነበር የሚገቡት:: እስከአሁን በሚኒሊክ ሪዮት አገር ይለቀቅ የሚለው ይህ ህዝብ አማራው ነው:: በቃ የሚኒሊክ ሪዮት ሳይክሉን ጨርሷል! በሰላም ተፋታ መፋታት ካለብህ!

የግርጌ ማስታወሻ:- በሚካኤልና ማሪያም ፎቶ ሳይቀር ታጅባችሁ ስድብን ለምታወርዱ ተሳዳቢዎች በእግዜር እላለሁ! ከአፍህ የስድብ ቃል አይውጣ እኛ ለመባረክ ተጠርተናልና ይላል ቃሉ::

ሊዲያ ዘውዱ

የማስመሰል ጦርነት Pseudowar

0

የደፂና የአቢይ የውሸት ጦርነት [Pseudowar]

ይህንን የውሸት ጦርነት ምን ብዬ ልሰይመው እያልኩ ሳስብ “ሲውዶዋር” Pseudowar የሚለው ቃል መጣልኝ። የዚህን ቃል ትርጉም ስመለከት በሚገርም ሁኔታ የዚህን ጦርነት ተብዬውን ጉድ በደንብ አድርጎ የሚገልፅ ሆኖ አገኘሁት። ዲክሺነሪ እንዲህ ይተረጉመዋል

A pseudo-war is a conflict which gives a government all the benefits of war but few of the problems.

ከጥቃቅን ጉዳቶች በተቀር ገዢውን መደብ የሚጠቅም ግጭት ማለት ነው።

ይህ የውሸት ጦርነት አቢይን በብዙ መንገድ ጠቀመ እንጅ ሃገሪቱዋን ወይም አማራን በምንም መልኩ አላተረፋቸውም። እንዲያውም አማራው በዚህ ውስጥ ዋና ታርጌትና ኢላማ ሆኖ ነው ያለው። ትህነግና ህዋሃትም የመቡዋጨር ያህል እንጅ ምንም አልተነኩም። እስካሁን ባለው ገፅታው ሲገመገም ይህ ሹኩቻ ፈረንጆች “Much a do about nothing” የሚሉት አይነት ነው።

የጊምቢውን የአማራ ጭፍጨፋ ተከትሎ የአቢይ አተዳደር ሳያስበው ጀኖሳይድርነቱ በአለም አደባባይ ተናኘበት፣ ደነገጠ፣ የመጨረሻ ማጨበርበሪያ ካርዱን ሳበ። “ጦርነት!!” ይሀው ነው።

ይህን ቀላል ጥያቄ እንጠይቅ እስቲ—–

ጦርነት ተብዬው ያስመዘገበው ምን ነገር አለ? ለአማራውም ሆነ ለሃገሪቱ ዴሞክራሲ?? ከአማራው ጥፋትና ከከተማዎቹም በጦርነት ስም መደብደብ በቀር? እርግጥ ነው አሁን ለመገምገም አይቻልም ምክንያቱት Pseudowar ሩ አሁንም እየተካሄደ ነው የሚሉኝ ይኖራሉ። እቀበላለሁ።

ግን እንዲያው በአንክሮ ለተመለከተ ሰው እስካሁን ማነው ሰለባው?? አማራው እይደለም?!!

ከጠዋቱም ጦርነቱ በብዙ አቅጣጫ ጥያቄ ጭሮብኛል። እንዲያው አንዳንድ ሰው የሰማውንና ያየውን ነገር ሁሉ ደርሶ መጠራጠር ወይም ሴራ የተለወሰ ነገር አድርጎ ማሰብ ይወዳል (conspiracy-monger)። አለ አይደል! ያጎረሱትን ዝም ብሎ አለመዋጥ! ያን ሰው ሆኜ ይሆን እንዴ የሚል ጥያቄ ጭንቅላቴ ውስጥ ሲደውል እንደነበር አልክድም። ለነገሩ እንኩዋንስ ያገኘነውን ሁሉ ውጠን ተጠራጣሪዎችም ሆነን እኝህን ጠ/ሚኒስትር አልቻላንቸውም።

አቢይና ህዋሃት/ትህነግ በዚህ ውጊያ-መሰል ሹኩቻቸው ያደረጉት ነገር ኪሳራና ትርፋቸውን መዝነው የጋራ ጠላታቸውን አማራንም በ equation ኑ ውስጥ አስገብተው ካሰሉ በሁዋላ planned with forethought ወይም በዘመኑ እንግሊዝኛ (Calculated Risk) እርምጃ ነው የወሰዱት። እስካሁን ደግሞ ግቡን እየመታ ነው።

የአቢይና ደፂ ጦርነት ትኩረት ከማስቀየሪያነቱ ባሻገር አንድ ትልቅ ተልእኮ አለው። በጦርነት ስም ወይም በማያስከስስ መንገድ አማራውን መጨረስ።

እስቲ እንኝህን ከእሳቤ ውስጥ እናስገባ

1/በጂምላ የተጨፈጨፉት አማራዎች ናቸው, ማይካድራ 524 አማራዎች።

2/ የአረጁና የጠላቶቻቸውን መሳሪያዎች የማይመጥኑ መሳሪያዎች የታጠቁ አማራዎች ከሁዋላ በትግራይ ልዩ ሃይል፣ ከፊት በመከላከያ መሃከል ተወርውረው ታርጌት የሆኑት አማራዎች ናቸው። ለብዙ መቶ የታጠቁ አማራዎች ጦር ግንባር መማገድና መጨፍጨፍ ምክንያት ሆኖአል።

3/ ሮኬቱም ወደ አማራ ከተሞች ነው እየተተኮሰ ያለው አስመራ የሚል አሁን አሁን ብንሰማም። የባህር ዳር ኤርፖርት እንደተመታ ሰምተናል

4/ ህዋሃትም መከላከያም በደንብ ያላቸውን መሳሪያ ተጠቅመው የቀለጠ ጦርነት ውስጥ አልገቡም። አንዱ ወገን ለሌላው ወገን የሚሳሳ ይመስላል። በተለይ ትግራይ ምንም ሳይዋጋ የያዛቸውን የአማራ ግዛቶች ዝም ብሎ ለቆ ወጣ ማለት ትልቅ ጥርጣሬ ውስጥ ሊከተን ይገባል

5/ በሁለቱ ወገኖች መካከል መናበብ አለ ብዬ የማምንበት ሌላው ምክንያት የተመለሱ የአማራ ግዛቶች ምእራብ ትግራይ ተብለው ለህዋሃት ሊመለሱለት ነው ወይም ኦሮሙማ ይውጣቸው ይሆናል። ለዛም ይመስላል ትህነጎች ምንም ሳይዋጉ ለቀው የወጡት።

6/ አቢይ ህዋሃትንና ትህነግን በአለም የቴረሪስት ግሩፕ እንዳይደመሩ የማይካድራውንም ጭፍጨፋ ትግሬዎች አደረጉ ብሎ አልፈረጀም። የመንግስት ሚዲያዎችም ዜናውን ከትህነግ ጋር አያይዘው ከመዘገብ ተቆጥበዋል።

7/ አሁንም አማራው የአቢይን ጦርነት እየተዋጋ ባለበት ሰአት እየታረደ መቀጠሉ። ትላንት በመተከል፣ድባጤ ቂዶና ከ60 በላይ አብዛኛዎቹ አማራዎች (ሁሉም አይደለሙ፣ ታርጌቱ ግን አማራው ነበር) ከአውቶብስ እንዲወርዱ ተደርገው ተጨፍጭፈዋል

8/ በአማራው ላይ በተለያየ ወቅት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመውና አስፈፅመው እጆቻቸው በደም የተጨማለቀ ሰዎችን ከስልጣን በማውረድ ስም ካንዣበበባቸው የህግና የህዝብ መአት ለማስመለጥ በግርግሩ በጠ/ሚኒስትሩ ሹም ሽረት መደረግ። ለምሳሌ የሽመልስ አብዲሳ፣ የደብረፅዮንና የተመስገን ጥሩነህ ከርእሰ መስተዳደርነት መገለል በወንጀል እንዳይጠየቁ በምክክር የሆነ እንጅ እነኝህ ሁለት ነፍሰገዳዮችን ሳይወዱ አቢይ ከስልጣናቸው የማውረድ እርምጃ አልወሰደም።

ይህ ጦርነት የጄኖሳይድን ወሬ ማፈኛ፣ ትኩረት ማስቀየሪያና በተለይም ደግሞ አማራውን መማገጃ እንጅ፣ ህዋሃትን ነቅሎ ለመጣያ፣ ወይም ትህነግን ማስወገጃ፣ ወይም በሃይል የተወሰዱትን የአማራውን እርስቶች ማስመለሻ፣ ወይም የመቀሌ ወንጀለኞችን፣ ህወሃትንና ትህነግን የማስወገጃ ጦርነት አልነበረም ያልኩባቸውን ምክንያቶች እስካሁን ከተመዘገቡት የጦርነቱ ውጤቶች ስናይ ውነትም ስሜት ይሰጣሉ ያሰኛል።

አያችሁ ወገኖቼ፣ እላይ እንድገለፅኩት ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ከጠላት ካምፕ የሚደርሱትን ጥቃቅን ጉዳቶችን ማስተናገድ የጦርነት አንዱ ስልት ነው። 20 ሰዎችን የማጣት Risk ወስዶ በመቶዎች ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ ጠላቶችንና ሰፈሮቻቸውን የመደምሰስ እርምጃ መውሰድ የተለመደ ነው (calculated risk)። በዚህ ጦርነት የህዋሃት ልዩ ሃይሎችና የትህነግ ሰራዊት አልተነኩም ማለት አይደለም። ለምሳሌ ከያዙዋቸው የአማራ ግዛቶች ሲለቁ አይተናል። የሞቱም አሉ። ነገር ግን ከከሰሩት ይልቅ ያተረፉት እጅግ ብዙ ነው። ተመለሱ የተባሉት የአማራ ግዛቶች ለአማራው አልተላለፉም።

ጦርነቱን የተለመደው የአቢይ ማወናበጃ ነው ባልኩ ጊዜ አብዛኛው ሰው፣ ለአማራው የሚቆረቆረውንም ክፍል ጨምሮ፣ ጦርነቱ ”አማራው ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው፣ በፌዴራሉ ሰራዊት/መከላከያ የታገዘ፣ በነመለስ ዜናዊ የተወሰዱበትን እርስቶቹን ለማስለቀቅ ያገኘው ወርቅ እድል ነው” እያለ ነበር የሞገተኝ። ከዚህ በፊት ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በተመሳሳይ ጎዳና ረጅም ርቀት አብረን ተጉዘናል። አሰራራቸው እስካሁን ያልገባው መቼም ይገባዋል ብዬ አልልም። ግን ጦርነት ብለው ማወጃቸው በአንድ በኩል ደስ አለኝ፣ ምክንያቱም ጠ/ሚኒስትሩ ህዝቡን ማሞኛ ካርዳቸውን መዘው ወደመጨረሳቸው መቃረባቸውን አበሰረኝ። በሌላ በኩል ደግሞ እኩይነታቸውን ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ በማየቴ ለሃገራችን ምንኛ አደገኛ ሰው እንደሆኑ መገንዘብ ቻልኩ።

አማራው በተለይ ለጦርነቱ ልዩ ሃላፊነት እንዳለበት እንዲሰማው እንዴት አደርጉ??

አማራውን የጦርነቱ ተካፋይ እንዲሆንም ጥሩ ቅንብር ተደርጎበታል። ትህነግ አጠቃ የተባለው የሰሜኑን እዝ ብቻ ነው ቢባል ኖሮ አማራው ብቻ መከላከያን የመቀላቀል ግዴታ አይኖርበትም ነበር ምክንያቱም የፌዴራል አካል ነውና የተጠቃው። ነገር ግን የጦርነቱ አላማ ሲጀመር አማራውን እግረመንገዳቸውን ለመጨረስ ስለነበር አማራውን የግዴታ በጦርነቱ እንዲሳተፍ የሚያደርጉ ምክንያቶችን አከሉበት። ለምሳሌ ያህል ትህነግ አጠቃቸው ከተባሉት ታርጌቶች መካከል የአማራ ክልል የሆኑት እነዳንሻም ተካተቱ። ዳንሻ የአማራ ክልል ስለሆነ እንግዲህ ብአዴን አማራውን ተነስ ክልልህ ተጠቅቶአል ብሎ ትእዛዝ ለመስጠት መንገድ ሆነው ማለት ነው። ነገሩ ውሎ አድሮ እንደታየው ግን የአቢይን ጦርነት አማራው እንዲዋጋለትና በዚያም እንዲያልቅ ነበር የተጠነሰሰው።

አማራው ምንም ሳያቅማማ ለምን መከላከያን ተቀላቀለ??

ልብ የሚሰብር ነገር ነው። የዚህ መንግስት ሸፍጠኝነትና ጭካኔ እንዲሁም ንቀት በአማራው ብሄር ላይ፣ ይህ ነው አይባልም።

አማራው ከመከላከያ ጋር አብሮ ትህነግን እንዲወጋ በተጠራ ጊዜ እሱ ያሰበውና ያለመው እርስቱ በዶ/ር አቢይ ሰራዊት እገዛ ሊመለስለት ነው ብሎ ነበር። ትህነግ ከአማራው ክልል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊወጣልን ነው ብሎ ነበር፣ በክልላችን መዋከብ ሊቀር ነው፣ ሁመራን ልናርስ ነው፣ ወልቃይት ወደ እናት ምድሩዋ ልትመለስ ነው፣ ጠለምትም ራያም ወዘተ ብሎ ነበር ያሰበው። የዋሁ አማራ ጎመጀ፣ ነፃነትን ለማየት በዱላም ዝመት ቢሉት ይዘምት ነበር።

ከጦርነቱ ጥንስስ በስተጀርባ ግን እኩይ ሰዎች እንደነበሩ አልተገነዘበም። በሰዎች ህይወት ቁማር የሚጫወቱ አመራሮችና ጄነራሎች እንደነበሩበት ትዝም አላለውም ነበር። እሱ የዋህና ይቅር ባይ ስለሆነ ጠ/ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት አስጨፍጭፈውትም እንኩዋን ያንን ረስቶ መሪው ለእርሱ እርስት ግድ ይሰጣቸዋል ብሎ አመነ። ይሄ የዋህነቱ ነው አማራውን የቀበረው!!!!!

እርካብና መንበር

ጠ/ሚኒስትራችን አማራው መስማት የሚፈልገውን ነገር አሰምተውት ነበር ትህነግን ከመግጠሙ በፊት። ትዝ ይለናል አይደል ይህ አሰራር???የእርካብና መንበርን ገፅ ኮፒ አድርጌ እንድታዩት ያህል ከዚህ በታች እዩት። “የሚፈልጉትን ነገር አያሳየህ ወደሚፈልጉት ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው” ከዚያም “በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” የሚለውን ተረት ተርትባቸው። ጠ/ሚኒስትሩ ይችን ዘዴአቸውን በአማራው ታጣቂ ላይ ሲጠቀሙ ምን አሉ? “ጀግናው የአማራ ታጣቂ/ገበሬ….” ብለው ትላንትና በኦነግና በኦነግ ሸኔ ያስገደሉትን አማራ አሁን ለጦርነቱ ሲፈልጉት ይቺን በማስመሰል የተሞላች ሙገሳና ሽንገላ በጆሮው አንቆረቆሩለት። ለነገሩ የሳቸው ጣፋጭ ንግግር ሳይሆን አማራውን ያዘመተው የተነጠቀው የእናት አባቶቹ፣ የአያት የቅምአያቶቹ፣ የራሱም ትውልድ እርስት ይመለሳል የሚል ተስፋ እንጂ። በዚያ ላይ ደግሞ ብአዴን አለ፣ የአቢይ ሎሌ፣ አማራውን ክተት ብሎ የሚያዝለት። ስለዚህ አማራው ለወልቃይት፣ ለመተከል፣ ለጠለምትና ለራያ ሲል ዘመተ። ምን ያህሉ እንደተሰዋ ገና በውል አልታወቀም ። በውል የታወቀ ነገር ቢኖር አማራው መሃል የገባ የጭዳ ዶሮ እንደነበር ነው።

ጠ/ሚኒስትሩ እርስቶቹን በኦሮሙማ ፕርጀክት ሊውጡዋቸው ይሆን?

እነኝህ የአማራ እርስቶች ከትህነግ እጅ ተለቀቁ። ትግሬው የጨረሰውን ጨርሶ ወደቤቱ ወደትግራይ ፈረጠጠ። ወልቃይትም ራያም ሌሎችም እርስቶች ተለቀው ለመጀመሪያ ጊዜ በ 29 አመት ትግሬ አልባ አየር ተነፈሱ፣ በአማራው ልዩ ሃይልና በመከላከያው ትብብር። ለጥቆም እንግዲህ አማራው እልል ማለት ጀመረ አማራው “እርስታችን ተመለሰ” “እርስታችን ተመለሰ” እያለ።

የዋህ አማራ ጠ/ሚኒስትሩ ምን ያህል ነውረኛና ሃሰተኛ ሰው እንደሆኑ አላወቀም። የስራ መመሪያቸው ህዝብን ማገልገል ሳይሆን፣ ህዝብን እያታለሉና እየደለሉ በጥቃቅን ጊዜያዊ ቁጣ ማብረጃ ቀናቸውን የሚገፉ ስው እንደሆኑ አላወቀም።

ጉድ እኮ ነው!!! የአማራውን ግዛቶች ጠ/ሚኒስትሩ ለአማራው የማያስረክብበት ምክንያት ምንድነው? እንኩዋንስ አማራው ደሙን አፍስሶላቸው ይቅርና በጦርነቱ ባይሳተፍም እንኩዋ፣ መተከል፣ ራያ፣ጠገዴ ወልቃይት፣ ጠለምት የአማራ ግዛት የነበሩበት ጊዜ እኮ እንደትላንት ቅርብ ነው። በአለም መንግስታት የፀደቀ፣ ይፋ የሆነ ካርታ በየቤታቻችን አለ። ነው ወይስ ጠ/ሚኒስትሩ በአማራው ግዛቶች ቁማራቸውን ሊጫወቱ ነው??? ይሉኝታ፣ ሃጢአት፣ ነውር፣ ወንጀል የማያሳስባቸው፣ ያለቦታቸው የተቀመጡ በቀን ቅዠት ውስጥ የሚኖሩ ጠ/ሚኒስትር። መቼም ህዝብን በቀጥተኝነትና በሃቅ መምራትን አያውቁም። አቁዋራጭ፣ ሸፍጥና ውሸት የሚያዋጣቸው ይመስል

ሴራና ስንፍና ከተጣመመ የወንጌል እምነት (የእምነት ቃል/Word of faith) ጋር የተላበሱ ጠ/ሚኒስትር

አሁን ላለንበት ጣጣ የተዳረግነው የእኚህ ሰው ስራቸውንና ቅደም ተከተልን አለማወቅ፣ ካላቸው ብልጣ ብልጥ የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ጋር ተደምሮ ባመጣው ምስቅልቅል ነው። ከመጀመሪያው ወደ ውጭ ከመሩዋሩዋጥ ይልቅ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉትን የላሉ ቁዋጠሮዎች ቢያጠብቁ ኖሮ ዛሬ እዚህ አንደርስም ነበር።

የጠ/ሚኒስትሩ ቁጥር አንድ አሰራር የጥፋት አካላትንና ወንጀለኞችን አቅፎ ከሁዋላ እየደግፉ ቆሻሻ ስራቸውን እንዲሰሩላቸው ማድረግ ነው። ትህነግ እሳቸው ስልጣን ከያዙ ጊዜ ጀምሮ በሰሜኑ አካባቢ ሲፉዋልል፣ ምሽግ ሲቆፍር፣ ሽብር ሲፈጥር ምንም ነገር አልተነፈሱም ነበር። ኦነግን ከነመሳሪያው ወደሃገሪቱ እንዲገባ ሲያደርጉ በአጋጣሚ አልነበረም። ጠ/ሚኒስትሩ ኦነግን በምን ሁኔታ እንደሚጠቀሙበት ከጠዋቱ ያውቁ ነበር። ኦነግ ወደ 20 የሚቆጠር ባንክ ሲሰብር ራሱን ማደራጃና ማስታጠቂያ የሚሆነውን ራሽን እንዲያገኝ ተፈቅዶለት ነው። በባንክ ዘረፋው ሰሞን ከጠ/ሚኒስትሩ የተሰነዘረ ግሳፄ ወይም በኦነግ ላይ የተሰማራ ህግ አስከባሪ ነበር? እንድም ኮሽታ አልነበረም። ከዛም በሁዋላ ኦነግሸኔንና ቄሮን አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደዘረገፉት በኦህዴድ/ኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ፋይናንስ አድራጊነት ሽብራቸውን እንዲቀጥሉ ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩና አባሮቻቸው ናቸው። እሳቸው ቤተመንግስት ቀለም ያስቀባሉ፣ ኦነግ፣ኦነግሸኔና ቄሮ ከትህነግ ጋር ሆነው ወንጀላቸውን ይፈፅሙላቸውል። ደሞም ሴራው በደንብ ሰርቶአል ምክንያቱም ምንም እንኩዋ አሁን ጥያቄ ውስጥ ቢገባም የኖቤል ሰላም ተሸለሚ ሆነዋል።

ታዲያ አሁንም ህዋሃትንና ትህነግን ማጥፋት ቀርቶ በማይካድራው ጄኖሳይድ እንኩዋን ተጠያቂ እንዲሆኑ በመንግስት ሚዲያዎች ስማቸውን ጠቅሰው እልወነጀሉዋቸውም። ምክንያቱም ለወደፊት ህዝብን እያሸበሩ ትኩረትን እንዲስቡላቸው ይፈልጉዋቸዋል። ጠ/ሚኒስትሩ በስራ አያምኑም፣ ሃላፊነትን በመውሰድ አያምኑም፣ የቃል እምነት እንደሚያስተምራቸው በመመኘትና በማውጠንጠን ነው አገርን ማስተዳደር የሚፈልጉት። ወንጀሎችን በህግ ማስወገድ እጅግ ያስፈራቸዋል። ስንት የኢሃደግ ወንጀለኞች እምባሳደሮች ሆነዋል። እነጌታቸው አሰፋን የመሳሰሉ ወንጀለኞች አሁን ድረስ ሳይነኩ ተቀምጠዋል።

ይህ ከወንጀለኞች ጋር፣ ከኢፍትሃዊነት ጋር ተለጥፎ የመስራት አባዜ በመንፈሳዊውም አለም እየተገበሩት ነው። ሃሰተኞች ነቢያትንና ሃዋሪያቶችን ከብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች ጋር ወጣቱን ሲበክሉ፣ ህዝቡን ሲዘርፉ፣ ጠ/ሚኒስትሩ ሽርካቸው ናቸው። ጤናማዋን ቤተክርስትያንና እውነቱን እያፈረጡ ሃሰተኞቹን የመቅደስ ዘራፊዎች በመድረክ ቆመው በሃይለ ቃል ሲያወግዙ የቆዩ ሰባኪዋችን ከወሮበሎቹ ሃሰተኞች ጋር ያስታረቁ መሪ ናቸው። ካውንስል የተባለው ጉድ ለፖሊቲካ አጀንዳቸው ማስፈፀሚያ ምእመናንን አስሮ እግራቸው ስር እንዲጥልላቸው የተመሰረተ ኢወንጌላዊ አካል ነው። ለሳቸው አጀንዳ አስፈፃሚ ነው።

እንደ ሁልጊዜው እኚህ መሪ ያለ ትህነግ፣ ህዋሃት፣ ኦነግ፣ ኦነግሸኔዎችና ቄሮዎች መንቀሳቀስ አይችሉም። ስለዚህም ህዝብንና አገርን ለማስፈራሪያነትና ለትኩረት መሳቢያነት ይጠቀሙባቸዋል እንጅ አያጠፉዋቸውም።

ይብላኝ ለአምራው የማንም ቁማር ቺፕስ (Gambling Chips) ለሆነው። የማንም መወራረጃና መቆራቆዣ ለሆነው።

አማራዎችና ፍትህ ፈላጊ ዜጎች የእነኝህን ሁለት ቀበጦች (ህዋሃትና ብልፅግና ፓርቲ) ማወናበድ ብዙ ትኩረት አትስጡት። የሚሰሩት አብረው ነው። የሚያስተሳስራቸው የጋራ ጠላታቸው አማራው ነው። ነገ በለቅሶና በይቅርታ እቅፍ ይተቃቀፋሉ።

አማራውን ከጨረሱት በሁዋላ እርስ በእርስ ይፋጫሉ። እስከዛው ግን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።

ዶ/ር ደረጀ ከበደ

ለአክአብ ተገለጥ!

0

ቤተክርስቲያናት ምእመናቸውን ይዘው ሲፈልጉ ምህላ፥ ፆምና ሱባኤ እያወጁ፤ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ እየናጠ ያለው የውስጥ የበዳይ ተበዳይ የዘር እና ሃይማኖት ቁርሾ ባላየ እንዳልሰማ ሆነው፤ ከራሳቸው አልፈው እግዚአብሄርን ሊያታልሉ ሲገበዙ ግዜ ጠብቆ የተጠመደ ቦንብ እየፈነዳ ፀሎቱም ምህላው ከሰማይ መልስንም መለኮታዊ ጣልቃ ገብነትንም ማስገኘቱ ቀርቷል፤ ሰማያት ተዘግተዋልና! ቤተክርስቲያን ባላየና ባልሰማ ሰውን ከማታለል አልፋ እግዜሩንም ልታታልል ስትጥር አቅምና ጉልበቷ የነበረው ፀሎቷ እጅግ ማድረግ አቅቶት የነበራትን ብቸኛ ኃይል አጥታለች::

ኃይሏንና ክብሯን የወሰደባት ደግሞ ኮረብታማ ነገር ስታይ ከክብሩ ቀኝ ካስቀመጣት ስፍራ ሸርተት እያለች ብቻዋን ያለ ባሏ ልታይ ልታይ እንድትል የሚያደርጋት አስጢናዊ ባህርይዋ ያደገባት ስለሆነ ነው:: ፀሎትና ምልጃዋ ማለትም እጣንና ሽቱ የተሰጣትን ይዛ ሄዳ ቤተ መንግስት ውስጥ ከሰል የምታነድ ስለሆነች ነው::…….”የሰማይን መንግስት ተጠባበቂ” “እመጣለሁ” “የኔ መንግስት ከዚህ አይደለም” የሚሉ ብዙ ብዙ ደብዳቤዎች እና መልእክቶች አሉ ባሏ የሚላት:: ነገር ግን እርሷ ከልጅነቷም አታላይና ወስላታ ሚስት ሆና ውሽሞችን አብዝታለች:: ከሄደ ከመጣው መንግስት ጋር ሁሉ ጋር. አደባባይ ወጥታ ትጣቀሳለች!

የአደባባይ ሚስጥር የሆነው ቤተ እምነቶች ባጠቃላይ ጓዛቸውን ጠቅልለው መንግስት ቤት መግባታቸውና ፀሎታቸው ይሁን ምህላቸው፥ ፆሙ ይሁን ፀሎቱ፥ ውግዘታቸው ይሁን እቀባቸው በመንግስት ተቃኝቶና ተፈቅዶ ሲያበቃ ነው ወደ እግዜሩ በምእመኑ እንዲደርሰው አማኞችንም በቃል ባለ አቋም ሳይሆን በbrainwashing tactic “ለበላይ ተገዛ” ይላል ቃሉ በሚል ጭፍን አስተምሮ ህዝቡን ያስታሉ:: ልክ ለበላይ ተቀማጮች condition set ያላደረገ ይመስል:: ቃሉ በበታች ያለን እንድንገዛ የሚያዘን በበላይ ያለው ገዥም እንደቃሉ ካስካላስጨነቀና እስካላስቆጣ ድረስ ብቻ ነው::

“እናንተም ጌቶች ሆይ፤ ለባሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የእነርሱም፣ የእናንተም ጌታ የሆነው በሰማይ እንዳለ፣ የሰውንም ፊት አይቶ እንደማያደላ ታውቃላችሁና አታስፈራሯቸው”ኤፌሶን 6:9

“ጌቶች ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና ለባሪያዎቻችሁ በጽድቅና በቅንነት አድርጉላቸው። ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ።” ቆላሲየአስ 4:1

እዚሁ ፌስቡክ ላይ ጨምሮ በቤተ እምነት የሚነገረውና የሚሰበከው ለእኛ ብቻ ለበላይ የመገዛት ጫና እንዳለብን ነው:: ሆኖም የእግዚአብሄር ቃል ግን ለበላዮችም ያስቀመጠው መስፈርት አለው:: መንግስት እነኝህን መስፈርቶች እስካሟላ ነው ህዝበ ክርስቲያኑም ሊገዛለት የሚችለው:: በመፅሃፍ ቅዱሳዊ እውነት ስንገዛ የበላዮችም በመፅሃፍ ቅዱሳዊው ስልጣን ቃል ስር እስከተገኙ ነው::

አሁን ግን አገራችንን የሚንጠው ችግር በቀላሉ በምህላና ፀሎት ሱባኤያችን ያልተመለሰበት ምክኒያት አገሪቱን የናጠ ያለው የዘር ቁርሾ ቋት በክርስቶስ ባልነው ቤት ውስጥ ሃሳቡ መስተናገድ ብቻ ሳይሆን ስፍራ አግኝቶ እየተተገበረ በመሆኑ ነው! የእገሌ ዘር አይፀድቅም ከሚል ምፀት እስከ “የእንትና ነፃ አውጪዎች” ነን ባዮች፥ በክርስቶስ እንኳን ነፃ ያልወጡ ነፃ አውጪነትን ሲገበዙበት፤ በቤተ ክርስቲያን ጥንስሱን ጠምቀው ለመጠጣት በቅቶ መንክራትና ፓስተራትን ስላሳከረ ነው::

ጠንሳሾችና በዚህ የጥላቻ ጉሽ ጠላ የሰከሩ ባለካባና ቆብ ፤ የተለሰኑ መቃብሮች ቅራሪያቸው ለልጅ ልጅ ሊተርፍ በየመቅደሱ ቅድስትና መድረክ ላይ ጠላውን እየተጎነጨ ቋሚ ስለበዛ ነው:: ከማሰሮው ሳይጎነጭና ሳይስማማ በጠልተኝነት ጠላ ካልተሳከረ መድረኩስ የት ተገኝቶ::

ዛሬ ፆምና ፀሎት ቢታወጅ ምህላና ውግዘት ብናደርግ ሱባኤ ሲታወጅ ፀሎታችን እጅግ ማድረግ ሲያቅተው እንደ ፃድቅ ሰው ያለ ፀሎት ባለመፀለያችን መሆኑን ተገንዝበን መጀመሪያ ራሳችንን ውስጣችንን እናንፃ!

ክፉ ነገር ጆሮን ጭው የሚያደርገው ነገር ሲሆን ቶሎ የሚያስቆጣም የሚያስደነግጠውም ህዝቡን እንጂ ሃይማኖት መሪዎችን አይደለም:: እነርሱ የህዝቡን የቁጣ ግለት ለክተው በዛው ልክ ሰፍተው የሆነ የሆነ ቃል ወርወር አድርገው ለይስሙላ ይማተባል ይፀለያል ይዘመራል ይዘለላል:: የመሪዎች ጩኸት ግለት በመለካት ስለሆነ ህዝቡም አሁን አሁን ከእነርሱ መስማትም ትቶታል:: ይህ ደግሞ መንፈሳዊ ቀውስን ፈጥሯል:: አደገኛ ነው!

በእምነት ቤት ላይ በመሪነት የተሰየሙ ሰዎች ጩኸት ሊሰማ ያልቻለው እነርሱ ከአክአባዊው መንግስት ጋር ተዳብለው ለበኦል እየሰገዱ ስለሆነ ነው:: የነኤልዛቤልን ዛቻ ፈርተው በሌላ ቀንበር ሊያዙ ጎንበስ ያሉና ቆባቸውን ያወለቁ ሆድ አምላኩዎች ስለሆኑ ቤተክርስቲያን ሃይሏን አጥታለች:: ለባቢሎናዊቷ መንግስት ለጠፈሯ ንግስት ቂጣ ጋጋሪዎች የባቢሎን ምርኮኞች ስለሆኑ ነው:: ንጉሳቸውን ትተው ኬክ ጋግረንላት ርሃብ የምታርቅልን ቂጣ ጠፍጥፈንላት ሁሉን የምታስገዛልን እጣን አንቦቅልቀን በግብዣዎቿ ፊት ወንበር የምታሰጠንን ምድራዊቷን መንግስት እንፈልጋለን ስላሉ ነው:: “አባታችን ሆይ”ን ትተው “እናታችን ሆይ በምድር ያለሽው ከስልጣንሽ አቋድሽን የለት እለት እንጀራችንን ስጪን” እያሉ ለmystery Babylon ጎንበስ ቀና ስለሚሉ ነው::

በእውነተኛ በእግዚአብሄር መንፈስ የሚነዱን ሰዎች ይህንን የጥፋት ተባባሪ ጠላ ጠማቂነቷን የተቃወሙ እና ለባኦል አንሰግድም ያሉ ደግሞ ግዞተኞች ሆነዋል:: በብዙ መከራና ስደት ርሃብና ጥማት ሲያልፉ፤ የቤተክርስቲያን ላይ ተሹመው ቆብ ደፊ ፓስተራት መንክራት ግን በብዙ ሚሊየን ብር በሚያወጣ መኪናዎች ሲንፈላሰሱ….. ሱፍና ቀሚሳቸውን በመልክና ባይነት በዲዛይነሮች ሲያሰፉ ለአክአብ ወንበር አሟቂዎች ሲደረጉ ለባኦል አንሰግድም ያሉቱን ግን በሰይፍ ስለት አብራ አስጨፍጭፋለች::

መንግስት የቤተክርስቲያንንም ክብር ደርቦ መጎናፀፍ ፈልጎ በዚህ በኩል “ካውንስል” በሚል ስም በዚያ ደሞ “እርቅ” በሚል ስም ወደራሱ አምጥቶ በቤተ መቅደስ እቃ የሚጠጣና የሚሳከር ሆኗል:: በመቅደስ ጠላውን ሲጠጡ የለመዱ ደግሞ ቤተመንግስት ገብተው ሲጎንጩት ለእነርሱ ክብር እንደሆነላቸው ሁሉ ታብየዋል:: አብይን እንደ መሲህ ማቆላመጥን ተያይዘውታል::

የናቡቴን እርሻ ሲወስድ ዝም ብለዋል:: የፈለግሁትን ሳደርግና የናቡቴን የአባቶቹን ርስት እወስዳለሁ ስል ተው ከተባልኩኝ አልጋዬ ላይ ተኝቼ አለቅሳለሁ የሚል ህፃንን ንጉስ በነኤልዛቤልና በባኦል ነብያትነት በገቡ የቤተክርስቲያንን ክብር በሸጡ የእመነት ቤቶች መሪዎች ተው ባይነት ሳያገኝ ህፃኑን ንጉስ አክአብን እሹሩሩ ይላሉ:: ናቡቴ እርሻውን እንዲቀማ ሲደረግ፥ ቤቱ ሲቃጠል፥…….”ናቡቴም አክዓብን፡— የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ።” ስላለ በደለኛ ሲደረግ ዝም ይላሉ፥ የግፍን ደም ምድር ስትጠጣ መኃል እንደ ካህንነታቸው ገብተው ይህ ነገር ልክ አይደለም ማለት ያልቻሉ ……ኃይለ ቢሷ ቤተክርስቲያን ጥግ ይዛ ባላየ ታልፋለች::

ህዝብ አምላክ እንደሌለው ሰሪው እንዳላበጀው እየተገፈተረ በሻሸመኔ፥ ዝዋይ፥ አሩሲ፥ በጉራፈርዳ፥ ጊምቢ፥ ቡራዩ፥ ለገጣፎ ፥ ቤኒሻንጉል ሰው እነ ቆሎ ሲረግፍ እርሻው ሲወሰድ፥ ቤቱ ሲቃጠል ፥ አንገቱ በካራ ሲታረድ፥ ቤተክርስቲያን ባላየ እያለፈች ናቡቴን ጥፋተኛ እያደረገች ይልቁን ለመንግስት ልታረጋጋ መኃል የምትገባ የገዢዎች ልዝብ በትር ሆናለች:: የናቡቴ ሞት ግፍ ነው እንዳትል ስም ስታወጣና ስትፈላሰፍ ያለፍርድ ደም ከመንግስት እጅ እያስታጠበች ታደርቃለች:: ጮኻ የለም ይሄ “የናቡቴ እርሻ ነው ግፍ ነው” እንዳትል የአክአብ ሎሌ ሆናለችና!

ሰማይን የዘጋ ምናልባት የጥቂቶች ለአክ አብ ያልሰገዱ ቅሬታዎች የነኤልያስ ጩኸት ይሆንን? ምን ይመስልሻል ቤተ ክርስቲያን?

ከመንግስት ጉያ ውጪና የራስሽን የብቻ ድግስ አቁሚና ወደ መኃል ጥናውን ውስጂ እሳቱን እጣኑን ጨምሪና ይዘሽ ወደ ህዝቡ መኃል ሮጠሽ ግቢ! ይህንን መቅሰፍት አስቁሚ! ስለህዝብ ተማፀኚ! ስብከት መድረክ ማሞቂያ የማድረግሽን ግድፈት ተይ! ካህናቶችሽን በህዝብና በፈርኦን መሃል አግቢ!

በህግ ለተገባች ውሽምነት ያስጠላል! እንደ ተተውችና እንዳልተፈገች ሆነሽ፤ ካየሽው ሁሉ ጋር እንደ ሜዳ አህያ የፍትወቷ ግዜ እንደደረሰ መሆኑን ተይ ይልሻል ጌታሽ! ተይ! ቤተ መቅደሱም ሊፈርስ ህዝብም በግዞት ባቢሎን ሊወርድ ነው! ተይ! ንቂ!

ዛሬ “ጴንጤው” ንጉስሽ ጦር ሲሰብቅ ልጆችሽ ደግሞ በጥራዝ ነጠቅነት ያሳደግሻቸው ያንቺን ቅራሪ ዞር ስትይ ፉት እያሉ ያደጉቱ፤ በየፌስቡኩ ቃል ከእግዚአብሄር እየሰረቁ ዝም ብሎ መረገጥ ነው፥ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ ይህች ነች፤ እያሉ ለፍትህ የመጮህ አቅም የሌላቸው አቅመ ሰላላ ሆነዋል:: ፅድቅን መስበክ የማይችሉ ጉልበታቸው ባንቺው ጉሽ ጠላ የላላባቸው፤ አለምን በራሷ አልባስ መብራትና ጭስ ሊያስገርሟት ዜማ የሚሰርቋት አጓጉል ሆነዋል:: ትምህርቷን ኮርጀው በእግዚአብሄር ቃል አሽተው ሊያመናፍሱ ከባቢሎንን ከሩቅ እሩቅ ምስራቅ አምጥተው አሜንን እያሳከሉ ይተርካሉ::

ቤተክርስቲያን ሆይ:- የምትደልይው ሲልሽ በቀብድ የምታሲይዠው ይህ ህዝብ አምላክ አለው:: እድል ፈታዬ ነው የሚለው አምላክ አለው! ጭራሹኝ በግዞት ከእጅሽ አውጥቶ ሊያስማርክ ካለው ጥፋት ቶሎ ካለሽበት የመንግስት መደብ ተነስተሽ አቧራሽን አራግፈሽ ወደ ስፍራሽ ተመለሽ:: ዛሬውኑ እስራትሽን ከመንግስት የተዋደቅሽበትን ገመድ ከአንገትሽ ፈትተሽ ወደ ቦታሽ ተመለሽ! ከመንግስት አልጋ ውስጥ ውጪ! ወደ ክብርሽ ዙፋን በሰው ወደ ተናቀ በእግዚአብሄር ግን በከበረው የማእዘን እራስ ወደ ተመሰረትሽበት ድንጋይ ቶሎ ተመለሽ! ሙሽራ ያለ ጌጧ ድሮም ማስጠላት እንጂ ውበት አይሆንላትም! ሚስት ውሽምነት ስትገባ ነውር ነው!

ኮብልይ! ሮጠሽ ቶሎ ውጪ! መንጋውን አስመልጪ! በአንቺ ውስልትና መንገድሽን ለተማሩ ሁሉ ምሳሌ ትሆኚ ዘንድ ምናባት ከጥፋት ማምለጥ ቢሆንልሽ፤ ከባቢሎን ልጅ ጋር የተቀመጥሽ የፂሆን ልጅ ሆይ ኮብልይ!

የጦርን አታሞ የሚመታውን ህፃኑን ንጉስ አክአብን ተው በይው! ታሪክሽ አብሮ ጎዳፊ ነው! ገፅታውን ባንቺ ገንብቷልና!

ስለ ለናቡቴ ጩሂ! ለአክአብ ተገለጪ! ይህ አይደረግም በይ!

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችን ጋር ይሁን።

ሊዲያ ዘውዱ

ብልፅግና ወንጌልና ጠንቁ

0

ከቤተመቅደስ እስከ ቤተመንግስት

መንግስታት በቀንደ መለክትና በአዋጅ ሊያግዱት ሲገባ ቸል በማለታቸው በአመታት መካከል አድጎና መንድጎ፣ ብዙሃኑን አራቁቶ፣ ጥቂቶችን ሚሊኒየርነት ማማ ላይ የሰቀለ አስተምሮ ምን እንደሆን የሚገምት ሰው አለ? ታመው የሚማቅቁን ተፈውሳችሁዋል፣ የደህዩትን ባለጠጋዎች ናችሁ፣ አንድ ብር ስጡና እግዚአብሄር 10 ብር አድርጎ ይሰጣችሁዋል የሚለውንስ የተወላገደ ትምህርት ታውቁት ይሆን??? አማኝ የሚታመመውና የሚደሀየው ጠንካራ እምነት ሲያጣ ነው፣ አለበለዛ ክርስትያኖች አይደሀዩም አይታመመሙም የሚለውን ትምህርትስ ደርሳችሁበት ይሆን? የእግዚአብሄርን በረከት በግል ስጋዊ ጥቅም፣ በብርና በምድራዊ ቁሳቁስ ብዛት ብቻ የሚገለጥ፣ በካፒታሊስት ዋና መዲናዋ በአሜሪካ ተወልዶ በአፍሪካ ያደገውን የነ “ወንጌል ተጡዋሪዎች፣ ስራ ጠላቱዎች” ትምህርትስ ለይታችሁ አውቃችሁት ይሆን??

ትክክል ገምታችሁዋል። የብልፅግና ወንጌል ይሉታል። እኔ ግን “የብልፅግና ወንጀል” እለዋለሁ።

ስለብልፅግና ወንጌልና እስተምሮ በዚህ ጊዜ መፃፍ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ይህ የወንጀለኞች ዶክትሪን የፕሮቴስታንት ክርዝማቲክ አማኞችን በየአጥቢያ ቤተክርስትያኖቻቸው ከማራቆት አልፎ ዛሬ አገራችንን ለመምራት ቤተመንግስት የተኮፈሱ ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድንና ጥቂት ፔንጤቆስጤ የስራ አስፈፃሚዎቻቸውን፣ ይሀው አደገኛ ዶክትሪን፣ ተብትቦ እንደያዛቸው ግልፅ እየሆነ በመምጣቱ ህዝቡ ሃገራችን የገባችበትን አሌ የማይባል እጥፍ ድርብ ሰቆቃ እንዲረዳ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው። ስለመሪዎቻችን በተለይም ስለ ጠ/ሚኒስትሩ እንግዳ የሆነ፣ በአለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ የአመራር ክፍተት፣ ፍዘትና፣ ንዝህላልነት ላለፉት ሁለት አመት ከመንፈቅ ፀጉራችንን ስንነጭና ጥርሳችንን ስናፋጭ የቆየን በብዙ ሚሊዮን የምንቆጠር ዜጋዎች፣ መልስ ላጣንበት የአስተዳደር ውድቀታቸው፣ ምክንያት ከሆኑት ነገሮች መካከል አንዱ የሆነውን ይህንን የምናብ እምነት properity Gospel ተንትኖ መረዳትና ማስረዳት አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ እናውቃለን።

አያችሁ ብልፅግና ወንጌልን የሚያምን ወይም የሚከተል ሰው በሃዘን፣በደህነት፣በበሽታ፣በተፈጥሮአዊ መቅሰፍት ሰፈር መገኘት አይፈልግም። ያ ማለት፣ ምርት በአንበጣ ተወሮ ገበሬ ሲያለቅስ ብልፅግና ወንጌልን የሚከተል ሰው የተፈፀመው ውርጂብኝ እንዳልተፈፀመ፣ ቀና ቀናውን በማሰብና (Positive thinking) በእምነት (strong faith) ድልን በማወጅ አንበጣውም ይጠፋል፣ ምርቱም ይተርፋል ነው የሚለው። ጥቃቱም በህዝቡ አለማመን፣ ወይም ህዝቡ በእግዚአብሄር ላይ በደል ፈፅሞ ወይም እምነት ስለጎደለው የተፈጠረ የሰማይ ላይ ቅጣት ነው ብሎ ነው የሚያምነው። ስለዚህም አዘኔታ የለውም፣ ለተጎዳው ህዝብ መራራት አይችልም። ስለዚህ ነው መሪያችን እርጉዝ ሆድዋ ተዘንጥሎ ፅንሱ ሜዳ ላይ ሲጣል፣ ዝንብ የሞተ ያህል እንኩዋን ርህራሄ ያላሳዩት። ለጠ/ሚኒስትሩ ያ ድርጊት አልተፈፀመም ወይም በሰለባዋ እምነት ጉድለትና ሃጢአት የተነሳ የተፈፀመ ስለሆነ ለሳቸው ምንም ማለት አይደለም። በሰለባዋና በእግዚአብሄር መካከል ያለ ነገር ነው ብለው ስለሚያምኑ ህዝብ ያለቅሳል እሳቸው ያፉዋጩብናል።

ጁዌል ኦስቲን የተባለው በአሜሪካን አገር በጣም የታወቀ የብልፅግና ወንጌል ፓስተር በመፅሃፉ “Become a better you” ላይ ያለው አይነት ነው።

“Dwell only on positive, empowering thoughts toward

yourself, “You will see God’s blessings and favor in a

greater way.”

“ሃሳብህን በገንቢ ሃሳቦች ላይ ብቻ አድርግ ያን ጊዜ የእግዚአብሄር

በረከትና ሞገስ በህይወትህ በትልቅ መንገድ በሙላትህ ይገለፃል”

ብልፅግና ወንጌልን የሚከተሉ መሪዎች፣ የሌሎችን ችግር ማየት አይችሉም (No Empathy)፣ ችግር፣ በሽታና ደህነት ለእምነታቸው ተስማሚ የድል ትርክት ስለማይፈጥር፣ እያለ እንደሌለ መቁጠርና ጭንቅላታቸውን አሸዋ ውስጥ ቀብረው በምድር ላይ ያለውን እውነታ መካድ ይቀላቸዋል። እውነታው ግን አንታመምም ቢሉም ይታመማሉ፣ ሃዘንን ቢክዱም ሃዘን ይደርስባቸዋል፣ የተፈጥሮ አደጋን የለም ቢሉም የተፈጥሮ አደጋ ዙሪያቸውን ሲከሰት ያዩታል። ወይ አለበለዛ ዶ/ር አቢይ እንደሚያደርጉት ሃዘን በሰሜን ሲከሰት ወደ ደቡብ መፈርጠጥ፣ ፅንፈኞች ህዝብን ሲያርዱ ወደ ኢሳያስ አፈወርቂ ግዛት ማቅናት፣ በመተከል ከ 300 በላይ አማራዎችና አብረው የተገኙ አገዎችም በመንግስት በተደገፉ ፅንፈኞች ሲጨፈጨፉ ወደ ደቡብ ሄዶ ስለፓርክ ማውራት፣ ወሎ በአንበጣ ሲመታ እሳቸው በአሩሲ የለማ የእርሻ ማሳን መጎብኘት፣ Go kart እየነዱ፣ ኢላማ ተኩስ እየተለማመዱ መዝናናት፣ በጉራ ፈርዳ አማራዎች ሲታረዱ ስለሃዘኑና ጭፍጨፋው ላለማሰብና ላለመመስከር ዝምታን መምረጥ፣ በጠቅላላ አይንን ጨፍኖ አላየሁም ወይም አልሰማሁም ነበር ማለት ሊኖርባቸው ነው። ሌላስ? በጃልሜዳ ለብዙ አመታት በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያናት ተተተክሎ የነበረን መስቀል በአስተዳደሩ ትእዛዝ ከነበረበት ተነቅሎ አልሰማሁም ነበር ብሎ መሸምጠጥ፣ የቡራዩ ማፈናቀልንም አልሰማምሁም ነበር ማለትን ሊጠይቅ ነው። አልያማ ከለይ የዘረዘርኩዋቸውና ሌሎችም ያልተጠቀሱ በርካታ አሰቃቂ ወንጀሎችና የተፈጥሮ አደጋዎች በምድራችን በተደጋጋሚ አይናችን እያየ መከሰታቸውን የሚክድ ፍጥረት ከብልፅግና ወንጌል አማኞች፣ሰባኪዎችና ከ አሮሙማ ፖሊቲክስ አመራሮቻችን በቀር ማን ይኖራል? በሃገሪቱዋ እንብርት ላይ አየተፈፀሙ ያሉትን ጉዶች አላየሁም ነበር አልሰማሁም ነበር በሚል ፌዘኛ መሪ 110 ሚሊዮን ህዝብ ሲመራ እንግዲህ ከዛ በላይ መቅሰፍትስ አለ እንዴ? ጠ/ሚኒስትሩ በዋናነት ኢትዮጵያን የኦሮሞ ምድር ለማድረግ ካላቸው አጀንዳ ጋር የብልፅግና ወንጌል እምነት ፅንሰሃሳብ በአስተዳደር ስርአታቸው ገብቶ ታላቁንና የበለፀገውን የኦሮሞ የምናብ ምድር በቅዠትና በሰመመን እያጣጣሙ ወደፊት መሄድን እንጅ ሃዘንን፣ ድህነትን፣ ሞትን፣ የማሰቢያ ጊዜውም ልቦናም የላቸውም። ስለዚህ ለቅሶ ቤት ከመሄድ ሰርግ ላይ ቢገኙ ይመርጣሉ።

የጠ/ሚኒስትሩ ፀጥታን አለማስከበርና፣ የጥቃት ሰለባዎችን በጊዜውና በቦታው ተገኝቶ ችግራቸውን አለመጋራት፣ አለማፅናናት፣ አለመካስና ከሚመጡት ጥቃቶች አለመጠበቅ ምክንያት የብልፅግና ወንጌል እምነታቸው ብቻ ነው የሚል ካለ ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ የቀበረ ሰጎን መሆን አለበት። እንዳውም ላስረግጥ የምፈልገው ነገር ከብልፅግናውም ቅዠት ይልቅ የኦሮሙማ አጀንዳቸው፣ አማራን፣ አማርኛንና ኦርቶዶክስን የማጥፋት እቅዳቸው እጅግ የከፋና እንደሆነ ነው።

አንትያ በትለር (Anthea Butler) የተባሉ የስነመለኮት ፕሮፈሰር ስለፕሮስፔሪቲ ጎስፕል መሪዎች ሲናገሩ “ዶናልድ ትራምፕንና ጆዌል ኦስቲንን ያመሳስሉዋቸዋል። እንደ ፕሮፌሰሩዋ አባባል ሁለቱም ከአማኞች ትልቅ ቅቡልነት ያላቸው ናቸው፣ በስኬታማነትም ያምናሉ፣ ነገርግ ግን በወንጌል ቃል ላይ የተመሰረቱ ወይም የበሰሉ አይደሉም” ይላሉ። ሁለቱም ማለትም ዶናልድ ትራምፕና ጆዌል ኦስቲን እንደማንኛውም የብልፅግና ወንጌል ተከታይ፣ የአሸናፊነትን እንጅ የውድቀትንና የተሸናፊነትን ወሬ መስማት አይፈልጉም። ፕሮፌስሩዋ የበለጠ ግልፅ በሆነ መንገድ ሲያስቀምጡት ታዲያ፣ ትራምፕንና ኦስቲንን የመሰሉ የብልፅግና ወንጌል መሪዎች የጎርፍና የአውሎ ነፋስ ዜናዎች አይስማሙዋቸውም ምክንያቱም ከብልፅግና ወንጌል ዶክትሪናቸው ጋር የሚስማማ የድልና የፈንጠዝያ ወሬ ስለማያበስር። በዚያም ላይ የብልፅግና ወንጌል መሪዎች አደጋንና ክፉ ክስተቶችን አደብስብሶና አቃሎ የማቅረብ፣ ሰለባዎች የደረሰባቸውን አደጋና አካላዊ ጉዳት ደግሞ ከግንዛቤ ያለማስገባትና ከጉዳይ ያለመፃፍ ባህሪይ አላቸው ይላሉ። ደግ ደጉን፣ አሸናፊነትን፣ መበልፀግን፣ አዎንታዊ ስነልቦናን (እምነትን) ይዞ ለቅሶና ዋይታ የሌለባትን አሮምያን መገባት።

ልብ ብላችሁዋል? የኛም ጠ/ሚኒስትር አንትያ በትለር (Anthea Butler) የገለፀችው የጆዌል ኦስቲንና የዶናልድ ትራምፕን ጠባይና ተግባርን ኮፒ ነው ሲያሳዩን የኖሩት። የማፅናናት ቃል ከአፋቸው እኮ አይወጣም። በወሎው አንበጣ ወረራ ሰአት እሳቸው Go-kart እየነዱ ኢላማ ተኩስ ጨዋታ እየተጫወቱ ልክ እንደነ ኦባማና እንደ ሌሎች የሰለጠኑና ሃብታም አገር መሪዎች ለመሆን፣ ነገረ አለሙን ረስተው ይቡዋርቁ ነበር። በጣም የሚገርም አይነት መደንዘዝ ይላሉ ያ ነው እንግዲህ። እነኦባማ ቢጫወቱ ያምርባቸዋል። ኦባማ በኤኮኖሚ የተንኮታኮተች አሜሪካንን ከቡሽ ተረክቦ ሌት ከቀን ሰርቶ ሃገሪቱን ከሪሰሽን (Recession) ያወጣ ጀግና መሪ ነው። ቢጫወትም ያምርበታል። የኛ መሪ የተረከቡትን ሃገር ጥለው አንዴ ዱባይ ሌላ ጊዜ ደግሞ ኤርትራ የሚዞሩ፣ አገር መምራት አይደለም አንድ የጉራጌ ሱቅ ማስተዳደር የማያውቁ፣ ለካሜራና ለታይታ የሚንቀሳቀሱ፣ በብሄር ተበጣጥቃ የአንድ ብሄር የበላይነት በፈረቃ የሚለዋወጥባትን አገር ለፅንፈኞች አሳልፈው ሰጥተው አገር ሲታመስ እንዳልሰሙና እንዳላዩ የሚሆኑ መሪ ናቸው።

ብልፅግና ወንጌል በቤተክርስትያን

የብልፅግና ወንጌልን አሰራር በቅጡ ለተመለከተ ሰው፣ በውስጡ ያዘለው ትምህርት ህዝብን በባዶ ተስፋና በወሬ፣ ያለውን እምነትና ንብረት የሚያስጥል፣ የመሰሪዎች “ በጨ ጠቆረ” ቁማር እንደሆን በቀላሉ ይረዳል። እንዲያውም የወንጌል አገልግሎት ሳይሆን አይን ያወጣ ዝርፊያ ነው ቢባል ማጋነን እይሆንም። ህዝቡ ያለውን ይሰጣል፣ ወትዋቹ ሰባኪ ግን የብር ፍቅር አስክሮት ጨምሩ በረከቱ በሰጣችሁት መጠን እንዲጨመርላችሁ ይላል። ብልፅግና ሰባኪው መድረክ ላይ ወጥቶ ህዝቡን ሲደልልና ሲሸጥ የጨረታ ገበያ አይነት ልፍለፋ መለፍለፍ አለበት። የምእመናኑን ልብ ለማባባት፣ ዝሩና አስር እጥፍ ታጭዳላችሁ ይላቸዋል። በኢየሱስ ስም የተለበጠ ወንጀል። በእስር ሊያስቀጣ የሚገባ ወንጀል። በካፒታሊዝም ስርአት የተለመደው፣ ግለሰቦችን በብዙሃን ላይ በገንዘብና በስልጣን የመቆለል ልምምድ (Individual achivement) የብልፅግና ወንጌል መሰረቱ ነው። ምን ማለቴ ነው? ብልፅግና ወንጌልን በመስበክ ሃብት ያካበቱ እንደነ ክራፍሎ ዶላር፣ እንደ ቲዲ ጄክ፣ እንደነ ኬኔት ኮፕላንድና እንደነጆይስ ማየር አይነቶች በአባሎቻቸው ላይ ያላቸው ተፅእኖ የአሽከርና የጌታ ያህል ነው። የእነኝህ ብልፅግናውያን አገልግሎትና እንቅስቃሴ ዋና የደም ስር የሆነው አባላቸው ደህይቶ፣ እነሱ ስመጥር ባለፀጋዎች ሆነዋል። በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ የሚንደላቀቁበትን ሃብት የሚሰጣቸውን ህዝባቸውን ራሱን መልሰው ሲንቁትና እንደ ጀሌያቸው ሲቆሩጡት ነው። የብልፅግና ወንጌል አስተማሪዎች ምእመናኑን በእምነት ከጌታ በረከትን እንዲጠብቅ ያስተምሩታል እነሱ ግን “እጅ በእጅ ፍቅር እንዲደረጅ” እንዳለው የሃገሬ ጉራጌ፣ በእምነት ሳይሆን በሚታይና በሚጨበጥ ጥሬ ገንዘብ (cash) ነው የሚደራደሩት። የአባሎቻቸው አስራትና ስጦታ ለሽቶ፣ ለሱፍ፣ ለጫማ፣ ለውድ መኪናዎች፣ ለግል ፕሌኖች፣ ለወርቅ፣ ለብዙ ሚሊዮን ዶላር ቤቶችና ለወፍራም የግል ባንክ አካውንት ነው የሚውለው።

ስለብልፅግና ወንጌል ማንበብ የጀመርኩት ከብዙ አመታት በፊት ነበር። ከ 20 አመታት በፊት አሜሪካ በብልፅጋና ወንጌል ቴሌቪዢን ሰባኪዎች (Televisionpreachers/Teleevangelists) ቁማርና ወንጀል ታምሳ በነበረበት ጊዜ እኔ እዚሁ አሜሪካ አሁን የምኖርበት ስቴት ነበር የምኖረው። እውቅና የነበራቸው የብልፅግና ወንጌል አስተማሪዎች አንድ በአንድ ወደላይ እንደወጡ እንደ ሉሲፈር ወደታች የተወረወሩባቸውን ወቅቶች በደንብ አስታውሳለሁ። ከፀጋ ከወደቁት የዶክትሪኑ አስተማሪዎች አንዱ የሆነው ጂም ቤከር የምእመናንን ገንዘብ ወደግል አካውንት በማዘዋወር ተከሶ ከሚወዳት ሚስቱ ከታሚ ቤከር (ወደ ጌታ ሄዳለች ከብዙ አመታት በፊት) ተለይቶ በ48 አመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበት ወደ እስርቤት ሲላክ ቴሌቪዥን ላይ ተጣብቆ የተከታተለው የአሜሪካ ህዝብ ቁጥር ቀላል አልነበረም። በሁዋላ ግን የጂም ቤከር ቅጣት በጥሩ ጠባይ ተቀንሶለት ከ 8 አመታት በሁዋላ ተፈታ። ያ ዘመን የብልፅግና ወንጌል ቴሌቪዥን ሰባኪዎች ዙሪያ ገፃቸውን በህዝብ ቁጣ ተከበው የነበረበት ዘመን ነበር። ሌላው ትልቅ የመነጋገሪያ ርእስ የነበረው የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ ኦራል ሮበርት በ 1987 በህዝብ ፊት፣ በህዝብ መገናኛ ወጥቶ “እግዚአብሄር በአንድ ወር ውስጥ 8 ሚሊዮን ዶላር ካልሰበሰብክ እገድልሃለሁ ብሎኛልና እባካችሁ ገንዘብ ስጡኝና ከሞት አድኑኝ” ብሎ ተናገረ። መቼም የአሜሪካን ህዝብ የዋህም ሩህሩህም ነውና የተባለውን ገንዘብ በተባለው ጊዘ ሰበሰበለት። የሚገርመው ግን ያም በቂ አይደለም ብሎ ሌላ 8 ሚሊዮን ብር እንዲሰበስቡለት የጠየቀበት ሁኔታ ነበር ያለው። እግዚአብሄር ብር ካላዋጣህ እገድልሃለሁ ብሎኛል ማለቱ በማያምኑ መካከል ሳይቀር መሳለቂያ ነገር ሆኖ ነበር። ከዛም ወዲህ በተለያዩ ወቅቶች የብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች እንደነ ቢሾፕ ላንግ (ነፍስ ይማር)፣ ሮበርት ቲልተን፣ ጆዌል ኦስተን፣ ቲዲ ጄክ፣ በኒሂን፣ ክራፍሎ ዶላር፣ ጆይስ ሜየርና ሌሎችም በርካታ ብልፅግናውያን የአገልግታቸውና የእለት እለት እስረሽ ምቺው ህይወታቸው ጉዳይ ለትልቅ ምርመራ (Scrutiny) ተዳርጎ ነበር።

መቼም ምን አለፋችሁ በወንጌል ታሪክ ውስጥ በጴንጤቆስጤና በሌሎችም ክርዝማቲክ ቤተክርስትያናት ውስጥ በተለያየ ወቅት ከተነሱት ሃሰተኛ ትምህርቶች ሁሉ አንደ ብልፅግና ወንጌል (prosperity Gospel) አማኙን ህዝብ ከምድር ዳርቻ እስከምድር ዳርቻ የጎዳ ትምህርት የለም። ዛሬም እየተራባ ነው። ብልፅግና ወንጌል የማያሻማ ስርቆት ነው። ስለዚህም ይህ የአጭበርባሪዎች ትምህርት በብዙ መንገድ ቤተክርስትያናት ብቻ ሳይሆኑ መንግስትም ሊከታተለው የሚገባ ነገር ሆኖ ሳለ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከልካይ ስላላገኘ ከአመት ወደ አመት እየሰፋና እያደገ ነው የሄደው። እውነትን ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን አገልጋዮችም ጭምር ይህንን ትምህርት በሃገራችን ህዝብ መሃከል የሚዘሩ አጭበርባሪ ሰባኪዎችን ሁሉ በአንድነት እንዲያወግዙም ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ብልፅግና ወንጌል ከየት መጣ እነማን አመጡት?

የብልፅግና ወንጌል ፅንሰሃሳብ የተፈጤረው የእምነት ቃል (Word of faith) ከተባለ ትምህርት ነው። የእምነት ቃል በጭሩ አንድ አማኝ ቀና ቀናውን በማሰብና በእምነት ከፈጣሪ እንዲደረግለት የሚፈልገውን ነገር በንግግር/በአንደበቱ በመናዘዝ/በመናገር በአእምሮውም ሳይጠራጠር በመቀበል የልቡን መሻት ሊያገኝ ይችላል ብሎ የሚያስተጋባ ሀተታ ነው። ይህ ዱቄት እንኩዋን መያዝ የማይችል ወንፊት ትምህርት/እምነት በአጋጣሚ ከሚሊዮን እንድ ካልሆነ በተቀር የማይፈፀም የቅዠት ነፀብራቅ ነው። የእምነት ቃል (word of faith) በ 20 ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ በክርስማቲክ ጴንጤቆስጤዎች ጎራ የተፈጠረ ትምህርት ሲሆን ትምህርቱ እግሮች አውጥቶ እንዲሮጥ ያደረጉት ወስላታ የእምነት አስተማሪዎችና መሪዎች አሉት። ከነዚያም ውስጥ ኬኔት ሄገን የተባለው ሰው የትምህርቱ አባት በሚባል ይታወቃል። ነገር ግን ከእሱ በፊት የቃለ እምነትን መሰረት የጣለው ፋይነስ ፓርከርስት ኩዋምቢ (Phineas Parkhurst Quimby (1802-1866) የተባለ ሲሆን ፋይነስ ለኬንዮን፣ ኬንዮን ለኬነት ሄገን እንዳስተላለፉት ነው የሚታወቀው። የእምነት ቃል “የሰው እምነት እግዚአብሄርንም ያዘዋል ነው የሚለው። በዛም አባባል “”እምነት” ከእግዚአብሄር ውጭ የሚሰራ ራሱን የቻለ ሃይል ያስመስለዋል። እውነታው ግን ሰው እምነትም ኖሮት የጠየቀውን ወይም የፈለገውን ከእግዚአብሄር ላያገኝ ይችላል። ወይም “የፈልጉትን ሰጣቸው ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ” (መዝሙር 106: 15) እንደሚል አንዳንዴ የፀለይንበትን አግኝተን ነገር ግን ጥቅሙ ሳይሆን ጉዳቱን እናጭዳለን። የ ”ቃለ እምነት” ወይም “የእምነት ቃል” አስተማሪዎች በቃሉ ላይ ከመመስረት ይልቅ እግዚአብሄር በተለየ መንገድ ለእነሱ የሚገልጠው የተለየ የቃለ እምነት መገለጥ አለ እያሉ ነው ህዝብን የሚያጭበረብሩት። መፀሃፍ ቅዱስን የእነሱን አጀንዳ እንዲደግፍ እድርገው በመተርጎም ያው እንደሚታየው በህንፃ ላይ ህንፃ የሚገነቡ ቢሊዮነሮች ሆነው ቁጭ ብለዋል። መፀሃፍ ቅዱስን ቁጭ አድርገው በመገለጥ፣ አየን ወይም ሰማን በሚሉት መሰረት ዬለሽ ቅብጥርጥር ሰውን ይዋሹታል፣ይዘርፉታል፣ ያደሀዩታል፣ ያሞኙታል።

የቃለ እምነት (Word of faith) በጨረፍታ

1/ሰዎች ትናንሽ እግዚአብሄሮች ናቸው ምክንያቱም ሲፈጥሩ ሙሉ የእግዚአብሄርን ባህሪይ ተሰጥቶአቸዋል ይላል። ሰው በምድርንና በውስጡዋ ባሉት ላይ ትንሹ እግዚአብሄር እንዲሆን እንዲያዝና እንዲገዛ፣ እግዚአብሄር ስልጣኑንና ሃይሉን ሰጠው። እግዚአብሄርን የሰማዩን መንግስት ሲመራ ሰው ደግሞ ምድሪቱን ሊገዛ ማለት ነው (Capps, Authority in Three Worlds, pp. 16-17).

እውነታው ግን በሰማይም በምድርም አንድ እግዞአብሄር ብቻ ነው ያለው። ሰው መቼም እግዚአብሄር አልነበረም አይሆንምም (ዮሃንስ 17:3)። ከሱ በፊት ከሱ በሁዋላም ሌላ እግዚአብሄር አልተፈጠረም እይፈጠርምም (ኢሳያስ 43 : 10).

2/ እምነት በቃል የሚንቀሳቀስ ሃይል ነው። የሚጨበጥ የሚዳሰስ ያህል ነገራትን የሚያንቀሳቅስ፣ እግዚአብሄርን የሚያዝ ግፊ ነው።

እውነታው ግን እምነት በእግዚአብሄር ቃልኪዳኖች ላይ መታመን ብቻ ነው። (እብራይስጥ 11:1)። እምነት ብቻውን እግዚእብሄርን አያዘውም። እኛ የሰው ልጆች የማናውቃቸው ነገርግን እግዚአብሄር የሚያያቸው፣ የሚያገናዝባቸው ነገሮች ሁሉ ለጠየቅነው ነገር ከእግዚአብሄር ምን አይነት መልስ እንደምናገኝ፣ መቼ እንደምናገኝ ይወስናሉ። እምነት አለኝ ገንዘብ አምጣ የምንለው አምላክ አይደለም የምናመልከው።

ብልፅግና ወንጌል ከቃለ እምነት ጋር የተያያዘ ሆኖ ሳለ አንድ ልዩነት ግን አላቸው። ያም ልዩነት የብልፅግና ወንጌል ወሮበላዎች በእምነት ውስጥ ገንዘብን አስተዋወቁ። ለመጀመሪያ ጊዜ “የእምነትን ቅንጣት ዝሩ” ማለት የጀመረው ከላይ የጠቀስነው ኦራል ሮበርት የተባለው የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ ነበር። አያችሁ የእምነትን ቅንጣት የምትዘሩት በገንዘብ ነው ማለት ነው። አማኞች ለምን የእምነትን ቅንጣት በእምነት፣ ገንዘብና ወርቅ በሌለበት መዝራት አይችሉም?? ያቺ ለእምነት ቅንጣት የተጠየቀችው ገንዘብ ወደሰባኪዎቹ ኪስ የምትገባ ገንዘብ ናት። ያቺ ገንዘብ ቀላል ገንዘብ አይደለችም። ብዙዎቹን የብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች የግል ጄት ባለቤቶች እንዲሆኑ ያደረገች ያቺ የእምነት ቅንጣት (seed of faith)ብር ናት። በአሜሪካን አገር በ”እምነት ቅንጣት” ዝሩ ሳቢያ የናጠጡ የወንጌል ወስላቶች በአሜሪካን አገር በአንድ ወቅት በኮንግረስ ሳይቀር ገቢና ወጪያቸው እንዲመረመር ተደርጎ ነበር።

ብልፅግና ወንጌል ከሌሎች ሃሰተኛ ትምህርቶች ሁሉ የከፋ ነው ብዬ ያልኩበት ምክንያት ምንድነው?

የብልፅግና ወንጌል

1ኛ/ የእግዚአብሄርን መለዮና ባህሪይ ደልዞ የሌለውን ባህሪይ የሰጠዋል። እግዚአብሄርንና ምድራዊ ሃብትን ያዛምዳቸዋል። እግዚአብሄርና ገንዘብ ምን ያገናናቸዋል? ገንዘብ ለሰጡት ገንዘብ የሚሰጥ ላልሰጡት ደግሞ የማይሰጥ? ገንዘብ ከሰጡት ጤንነትንና ስኬትን የሚሰጥ፣ ገንዘብ ካልሰጡት ግን ግድ የሌለው? ለመሆኑ ይህ የእግዚኣብሄር ባህሪይ ነው? አይደለም (ማቴዎስ 19:23-24 ፣ 1 ጢሞቲዎስ 6:10)

2ኛ/ የእምነትን ምንነት፣ በአማኞች ህይወት ውስጥ የሚጫወተውንም ሚና ፍፁም ያጣምመዋል። የእምነት ቅንጣት (ዘር) ና ገንዘብ ምን አገናኘው? እምነት የእግዚኣብሄር ስጦታ ነው። እምነት ሰው ከእግዚኣብሄር ጋር የሚዋሃድበት መለኮታዊ ልምምድ ነው። በገንዘብ አይገኝም። በገንዘብ አይሸጥም፣ በገንዘብ አይለወጥም (ኤፌሶን 2:8)

3ኛ/ በደህነት የሚማቅቁንና በበሽታ የጎሰቆሎ ሰዎችን ኢላማ ያደርጋል።

ስለዚህም በአሁኑ ወቅት የብልፅግና ወንጌል ዋና መራቢያ ቦታ አፍሪካ ሆኖአል።በኢትዮጵያም በግልፅ ይህንን የሌብነት ወንጌል እየሰበኩ ህዝቡን የሚሰርቁ ሰባኪዎች አሉ። እነሱን በህብረት ማውገዝ ይገባል። ያላችሁን ሙዋጣችሁ ከሰጣችሁ ሃብታም ትሆናላችሁ፣ ጤና ትሆናላችሁ ፣ በሚል የቀረቻቸውን ቤሳና በእግዚኣብሄርም ላይ ያላቸውን እምነት ይነጥቃቸዋል።

4ኛ/ ብልፅግና ወንጌል የሚያበለፅገው ሰባኪውን ወይም መጋቢውንና የእርሱ ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች የሆኑትን ኣጃቢዎቹን ብቻ ነው።

ህዝቡ ግን ያለውን ለመጋቢው ወይም ለሰባኪው ሰጥቶ ላም አለኝ በሰማይ እናዳለ በባዶ ተስፋ አይኑን እንዳፈጠጠ ይቀራል።

5ኛ/ ህዝቡ ያለውን እየሙዋጠጠ ከሰጠ በሁዋላ በሰባኪው የተነገረው የሰማይ ብርና ወርቅ ሲዘገይና ሳይከሰት ሲቀር፣ ጮሌው ሰባኪ መልሶ እምነት ስለጎደለህ ነው፣ ሃጢትህን ስላልተናዘዝክ ነው ከእግዚኣብሄር ገንዘብ ወይም ጤንነት ያላገኘሀው ወይም ያላገኘሽው ብሎ ጥፋቱን በተዘረፈው (ችዋ) ደሃ ይላክካል።ይህም አሰራር ዋሾው የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ (ዘራፊ) የእኔ ጥፋት አይደለም ብሎ እንዲያሳብብ ቀዳዳ ከመስጠቱም በላይ ተዘራፊዎቹ የደረሰባቸውን ጥቃት በራሳችን ጥፋት ነው ብለው እንዲቀበሉና ወደ ህግም እንዳይሄዱ ያግዳቸዋል። የጥቃት ጥቃት።

6ኛ/ እግዚአብሄርን በፎርሙላ ማንቀሳቀስ ይቻላል ይላል። ልክ እንደ ሂሳብ ትምህርት የተደነገጉ የአሰራር ፎርሙላዎችን ለተከተለ ሁልጊዜ ወደተጠበቀው ውጤት እንደሚወስድ ሁሉ የብልፅግና ወንጌል ትምህርትም አንድ ሰው እምነት ካለውና ይሆንልኛል ብሎ እስካመነና በቃሉም እስከተናዘዘ ድረስ ወይም በአእምሮው የጠየቀውን ነገር ሲቀበል ማየት ከቻለ የጠየቀው ነገር ከእግዚአብሄር የሰጠዋል ይላል። ይህ ደግሞ ፍፁም ውሸት ነው። የእግዚአብሄር ምላሽ አወንታ ወይም አሉታ የሚሆንበት ምክንያት ሁልጊዜ ለሰዎች አይታወቅም። እግዚአብሄር ስራው በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ናቸው። እምነትም ኖሮን፣ በቃላችንና በስነልቦናችንም ተናዘን የጠየቅነው ነገር ላይሰጠን ይችላል። ወይም ገንዘብ ጠይቀን ጤንነት እንቀበል ይሆናል። እግዚአብሄር በፎርሙላ አይሰራም። ማንም አያዘውም።

አገራችን

የአገራችንን ምስኪን ህዝብ የሚግጡ የብልፅግናና የቃል እምነት (word of faith) ሰባኪዎች ደሃውን ህዝብ ሃብታም ትሆናለህ፣ ከበሽታህ በእምነት ትፈወሳለህ፣ ደህነት አይነካህም ከእንግዲህ እያሉ በጋጡት ገንዘብ ሚሊየነሮች ሆነዋል። እንዳንዶቹ ከየክልሉ ሌሎቹም ከዛው ከአዲስ አበባ የተጠራቀሙ የኢየሱስን ስም የሚሸቅጡ ነውረኞችና ዘራፊዎች ከፍተኛ ድጋፍ ከዚህ ከወንበዴ መንግስት ስላገኙ ያለምንም ፍራቻ ወንጀላቸውን እየፈፀሙ ነው። ዶ/ር አቢይ አህመድ የወንጀለኞች ሹዋሚ ጠ/ሚኒስትር ቤተመንግስታቸው ድረስ ከሚጋብዙዋቸው ውስጥ የቃል እምነቶችና የብልፅግና ወንጌል ሰባኪ አጭበርባሪዎች ይገኙበታል። እንዲያውም እነኝህ ዘራፊዎችና ጤናማ ወንጌል ሰባኪዎች ይቅር ተባብለው አንድ ማህበር እንዲጠጡ ባዘዙት መሰረት ከጥቂቶች በተቀር ካውንስል መስርተው በአንድ ተቁዋዳሽ ሆነዋል። ጤነኛዎቹ ተብለው ይከበሩ የነበሩ ሰባኪዎችና መጋቢዎች፣ ሃሰተኛ ነቢያትንና ሃዋሪያትን (እነሱው ናቸው ብልፅግናና ቃል እምነትን የሚሰብኩት) አቅፈው ስመው “ድሮም እኮ ልዩነታችን ጥቃቅን ነበር” “ስራቸውን እንጅ እነሱን አልጠላም”

የሚሉ ሰበቦችን እያዥጎደጎዱ በአንድ ላይ “በካውንስሉ” ስም ይሰራሉ። ጤናማ ዘማሪዎችና ሰባኪዎችም በካውንስሉ ስብሰባዎች እየተገኙ ፕሮግራማቸውን ያደምቁላቸዋ። ዛሬ “ሰው ትንሹ እግዚአብሄር ነው” የሚሉ ወሮበላዎች እድሜ ለጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ ወደ ከርቸሌ መጋዝ ሲኖርባቸው ምላሳቸውን እያወጡ ያላግጡብናል። ባለዲዛይነር ሱፎች ናቸው። ከየት አመጡት ገንዘቡን አይሰሩ አይነግዱ? ከምስኪን ደሃዎች፣ ከህመምተኞች፣ እምነተ ለጋዎች ኪስ ነው የሰበሰቡት።

መንግስቱም ወስላታ

መሪውም የማይታመን

ሰባኪውም ቂስ አውላቂ የሆነባት አገር እግዚኦ !!!!!!!!!!!!!!

ይህ ሴይጣናዊ ትምህርት በአሜርካም ሆነ በአፍሪካ እንደ ሰደድ እሳት የተሰራጨው በኢኮኖሚ በተጎዱት ህብረተሰቦች መካከል ነው። ምክንያቱም ግልፅ ነው። ደሃ ከደህነቱ የሚያላቅቀው ነገር አለ ከተባለ የትም ይሄዳል። ምንም ያድርግ ?። ህዝብ ሞኝ ስለሆነ ሳይሆን ቢጨንቀው ነው ብልፅግና ብልፅግና የሚሉትን ሰባኪዎች የሚከተለው። የብልፅግና ወንጌል ሰባኪዎች አፍሪካ ድረስ ዘልቀው ታዋቂ መጋቢዎችን እየተጠቀሙ በቀን ከአንድ ዶላር በታች ከሚያገኘው ህዝብ ሳንቲም ይቃረጣሉ። የዚህ ስህተተኛ ትምህርት አዛማቾች በቀጣዩ አለም በእግዚኣብሄር ዘንድ የሚጠየቁ ቢሆንም በምድር ደግሞ ብዙ ጥፋት ሳያጠፉ በፍርድቤትና በዳኞች ፊት ሊቀርቡ የሚገባው ነው። እውነትን የሚወድ ሁሉ ደግሞ ሊያወግዛቸው ይገባል።

1/What Is the Word of Faith Movement?

https://www.gospeloutreach.net/whatwordfaith.html

2/The prosperity gospel, explained: Why Joel Osteen believes that prayer can make you rich https://www.vox.com/identities/2017/9/1/15951874/prosperity-gospel-explained-why-joel-osteen-believes-prayer-can-make-you-rich-trump

3/Death, the Prosperity Gospel and Me

4/Hagin, Kenneth. The Midas Touch: A Balanced Approach to Biblical Prosperity. Broken Arrow: Faith Library Publications, 2000.

Hagin,Kenneth, Redeemed From Poverty, Sickness, Death. Garland, TX: Kenneth Hagin Ministries, 1993.

በዶ/ር ደረጀ ከበደ

”COME OUT OF HER”

0

We have seen previously different aspects of Babylon. Today, I present the last trait of it. Enjoy reading!

Educational and Pseudoscientific Babylon

Educational and Pseudoscience deception:- we can only consent to scientific discoveries and researchers if it only remains provable. The freemasonry belief system is brought to schooling system to dictate, Evolution theory, Darwinism theory, progressivism, the Heliocentric globe model Freemasonry pseudoscience theory, the sex ED sodomite transvestite abomination agenda, feminism flimflam, pro-choice baby-killing, critical race theory, etc. This is all theories of a feeble, wicked, godless man bringing his disbelief and evil worship through the educational faculties. It’s clear that this hypothesis has a spiritual agenda. Are we to let Luciferianism override over our faith in the name of education? What makes science, science is provability. If science cannot back itself with evidence, it’s junk. We should throw it out! The theories I mentioned above, even though school teaches them as theory, most by the time they are adults they believe and take that and run as if it is the truth, even though to this day the school itself labels it as a hypothesis.

Let’s be clear; science is not the problem. We love science! The PROBLEM is when science become influenced by philosophical thought. Then it is becoming a RELIGION. For me dictating the clock of doomsday under the guise of global warming is science pausing itself as God. The Bill and Melinda Gates Contraceptive Management, aka depopulation’ agenda is not science, but evil obscuring science. Mind you, neither Bill nor Melinda are medical doctors or in any medical field, so to speak and yet these guys are now sanctioning global vaccine. Why are Bill and Melinda gates the so-called computer guys involved in public health matter, vaccines and contraceptives? Why is Bill on TV 24/7 propagating about coronavirus, while he has zero qualifications in the medical field? Why is Greta Thunberg the flimsy little girl, who knows it all, preach us about the calamity of the universe? Where are the REAL scientists? Why aren’t they talk to us? Why do they hide behind Gerta? The extent of the pseudoscience hoax going is flabbergasting!

We know that Global Warming is a smokescreen to set a time for doomsday. Babylon Luciferians knows that their time has an end day; it counterfeits every event that is lying ahead in scriptural prophecy. The devil is a devout student of the word of God. He studies it left to right, to deceive. Recently, in New York City Union Square, a giant digital clock has been reprogrammed to count down the amount of time left to take action to prevent the worst effects of Global Warming from becoming irreversible. These Luciferian godless elitists, Global Warming doomsayers, set up a clock citing our world will be annihilated seven years from now. This is Babylonian philosophy, trying to dictate science with no provable evidence. Freemasonry pseudoscience manipulating educational faculties, pausing their theory as if it is truth, to force us all to conform with the terms they deem for our adherence, citing it’s for the common good of humanity! This endeavour makes science a religion, not exploration or research anymore. So, by this notion, we reject Luciferian pseudoscience! This is Satan bringing his theology fronting science. If science wants to play as God, we reject the idea, for it is science no more.

The counterfeit of last days.

Rapture – alien abduction.

Return of Christ – alien invasion.

Tribulation- Global Warming.

Dissimilar to the unsuspecting multitude, the Luciferians elitist are well aware and are readying themselves to the prophecy of the Bible to take place. They know the time will come soon, for celestial bodies plummet, weather to change drastically, earthquakes, wildfires, pestilence, plagues, will take place in chronological order as scripture foretold.

This modern atheist big bang, heliocentric globe earth, chance evolution paradigm, spiritually controls humanity by removing God or any sort of intelligent design and replaces purposeful divine creation with haphazard random cosmic coincidence.⠀⠀

By removing Earth from the motionless centre of the universe, these Masons have moved us physically and metaphysically from a place of supreme importance to one of complete nihilistic indifference.⠀⠀

If the earth is the centre of the universe, then the idea of God, creation and a purpose of human existence are splendid. But if the earth is just one of the billions of planets revolving around billions of stars and billions of galaxies, then the ideas of God, creation and a specific purpose for the earth and human existence become highly implausible.⠀⠀

So by repetitiously indoctrinating us into their scientific materialist sun worship, not only did we lose faith in anything beyond the Materia; we gain absolute faith in materiality, superficiality, status, selfishness, hedonism and consumerism. ⠀

If there is no God and everyone is just an accident, then all that matters is things that benefit ourselves.

Let’s be rooted in Him, soever we avoid falling for every deception thrown at us. The world is seized by an evil as scripture affirmed, hence why, we shall expect nothing good to come out of the Babylonian system.

‭“Remain deeply rooted in him; continue being built up in him and confirmed in your trust, the way you were taught, so that you overflow in thanksgiving.” Colossians 2:7‬ ‭

So how do we Christians combat this orchestrated deception?

What should we do as Christians about this catastrophic time and system ahead of us?

Minimize economic dependency:- We shall learn to live soberly and inexpensively, so we will maintain the strength to withstand the prosecution that will be set loose, soon unto humanity, specifically, Christians who will oppose identifying with the beast’s system. Read Matthew twenty-four in its entirety. They teach many of us in our church houses that we will be ruptured before all of this incident takes place, it’s okay if that is so, but I say, let’s hope for pre-trib while preparing for mid or post-trib. That’s what faithfulness means anyway.

Have no political affiliation:- We must abide by the living word, not by what leaders (church or secular) or media. If a pastor aligned himself to a particular group, political ideology, and secular leader citing doctrinal ties, break loose, stand firm and stand against it! We will do irreversible damage if we are to think that there is a political solution for our lives and the world. There is no political solution we are awaiting. If we are to believe otherwise, we are setting ourselves to the great deception of the Antichrist; he will emerge to the scene to offer the help we demand, just like that we will fall away forever. We don’t have a political problem that politics can fix; we have an issue of SIN and MORTALITY. We need a spiritual remedy, not political! Look at how many Ethio- evangelicals being lured by Abiy and US by Donald. Christians are marching behind these men, thinking these are agents of God, defender of the faith, and will offer them help for their problem. Many are trapping themselves in the Anti-Christ’s web already. Both Donald and Abiy are a false light that the devil disguises as an angel of light to execute his plan, with no possible objecting and discernment from the conservative Christian base.

We must be reluctant not to believe what Babylonian owned media regularly propagates. We need to choose who to pay attention to- the WORD or the World, our choice. We need to cross-check our spiritual leaders. When religious leaders are intertwining themselves in the affairs of politics, and when playing with strange fire doctrine of the devil, we then depart from them.

We must be conscious of the false prophet; often, who claim bizarre revelation of the word of God only to them; we must not flinch or wobble to their deceitful attempt. The word is revealed already. Concerned Apostol Paul writes about this issue for Galatians “But even if we or an angel from heaven should preach to you a gospel contrary to what we have preached to you, a curse be on him! As we said before, so say I now again, If any man preaches any other gospel unto you than that ye have received, let him be accursed.” 1:8-9

‭‭In another place, he reinforces the same advice and instructs:-

“For if he that cometh preacheth another Jesus, whom we have not preached, or if ye receive another spirit, which ye have not received, or another gospel, which ye have not accepted, ye might well bear with him.” 2 Corinthians‬ ‭11:4‬

Be vigilant; be watchful! Do not believe all spirits, but test it if whether they are of God.

Lastly, be reminded that Victory is ours in the end, this we know! Now is the devil’s hour (limited) we might be sobbing, however, remember that the last laugh is ours!

” Rejoice over her, O heaven, and you saints (God’s people) and apostles and prophets [who were martyred], because God has executed vengeance for you [through righteous judgment] upon her.” Revelation‬ ‭18:20‬ ‭

More time for scripture, less time for social media. More time to pray, less time feeding on what’s thrown for public consumption.

The grace of the Lord Jesus Christ, and the love of the Father, and the communion of the Holy Spirit, be with you all.

Lydia Zewdu.

POPULAR POSTS

MY FAVORITES

I'M SOCIAL

232,216FansLike
0FollowersFollow
68,556FollowersFollow
0SubscribersSubscribe