የአማራ ተማሪዎች አገረ ማርያሞ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እየተሰቃዩ ነው። በኦሮሞ አክራሪዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ ከትምህርት ገበታቸው ላይ እንደተስተጓጉሉና ማስፈራራትና እንግልት እየደረሰባችው እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
ተማሪዎቹ እስከአሁን ድረስ በሜዳ ላይ ተበትነው ከትምህርት ቤቶች ዶርምተሪ ታግደው የሌሊቱን ውርጭ እየተገረፉበት ይገኛል:: ወደ መጡበት እንሂድ ቢሉም መታገታቸው ታውቋል:: የጠፋ የንፁሀን አማራ ነፍስም እንዳለ ታውቋል:: በተለያዩ የምስል ቅንብሮች እንደታየው ከሆነ ተማርዎች በታላቅ ሰቆቃ ላይ ይገኛሉ:: መንግስት ለነገሩ እልባት መስጠት አለመቻሉ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ የራሳቸው ክልል መስተዳድር አዴፓም ምንም እርምጃ እንዳልወሰደ እስካሁን ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በተቻለ መጠን አማራዊው ወላጅ ልጆቹን ወደ ሌላ የአገሪቱ ክፍል እንዳይልክ ስንል እናሳስባለን! ወላጅ ቤተሰቦች ልጆቻቸው እንዲመለሱ አዴፓን ማስገደድ ይህኖርባቸዋል!!
ወደ ክልሉ ዩኒቨርስቲዎች መማር አለባቸው ለዚህ ዘመቻ ደግሞ የአማራ አክቲቪስቶች እና አክቲቬተሮች ዘመቻ መጀመር አለባቸው!
Comments are closed.